ለሸቀጦች ዋጋ ከፍ ዝቅ ማለት ምክንያት ሆኗል ተባለ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2003 ዓ.ም. June 13, 2011)፦ አባይን ለመገደብ ከህዝብ የሚሰበሰበውንና ከቦንድ ሽያጭ የሚገኘውን ገንዘብ መንግስት ወደ ካዝና ማስገባቱ ለዋጋ ግሽበቱ ጠንቅ ሊሆን እንደሚችል የኢኮኖሚ ተንታኞች ስጋታቸውን ገለጹ።

 

በ17 የሸቀጥ አይነቶች ላይ የቁጥጥር እዝ የተደረገ ቢሆንም ከወራት በኋላ በገሚሶቹ ላይ የተጣለው ገደብ ሲነሳላቸው በጥቂቶቹ ላይ እዙ መቀጠሉ በነጻ ገበያ ስርአቱ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እለት ከእለት እየጨመረ መሆኑን ባለሙያዎቹ አስረድተዋል።

 

ወትሮም ነጻ ገበያን ለመልመድ ሙሉ ፈቃደኝነት አልነበረም የሚሉት ምሁራን በኢህአዴግ ኩባንያዎች ቁጥጥር ስር የነበረው የገበያ ሂደት ፈተና ላይ የነበረውን የገበያ ውድድር በአሁኑ ሰአት ደግሞ “የኢህአዴግ ደጋፊ ነጋዴዎች ፎረም” በሚል የተሰባሰቡ አፍቃሬ መንግስት ነጋዴዎች የንግድ ቀጠናውን ክፉኛ እየረበሹት እንደሚገኙ ተገልጿል።

 

በስጋና በቢራ ላይ የተጣለው ገደብ በተነሳ ማግስስት በአስደንጋጭ ሁኔታ ዋጋቸው አልቀመስ ከማለቱም በላይ በገደብ ስር ያሉት ስኳርና ዘይት ደግሞ በገበያው ላይ ለአይን መጥፋታቸው የገበውን ሂደት ከቁጥጥር ውጭ ከማድረጉም በላይ የድብቅ ግብይቱን በከፍተኛ ሁኔታ እያስፋፋ ይገኛል።

 

ችግሩ መንግስት ባልተጠና መመሪያ በሚወስዳቸው እርምጃዎች በአብዛኛው ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የኑሮ ደረጃ ለሚገኘው ማህበረሰብ ክፍልን ኑሮ ክፉኛ እያቃወሰ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል። መንግስት በተለጠጠ መልኩ ባወጣው የልማት ግንባታ ሳቢያ በጀቱን ያለአግባብ መባከኑ ከሚያመጣው የዋጋ ግሽበት በተጨማሪ ግሽበትን ለመከላከል በሚል በብዛት ታትሞ ገበያ ውስጥ ያሰራጨው ገንዘብ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሚዛንና የህዝቡን የመግዛትና የመሸጥ አቅም ክፉኛ እንደጎዳው ባለሙያዎች ይናገራሉ።

 

አባይን ለመገደብ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ተቋማት፣ የመንግስትና የግል ድርጅቶችን ጨምሮ በርካታ ባለሀብቶችና የህብረተሰብ ክፍል እየተሰበሰበ ያለው ከፍተኛ መተን ያለው ገንዘብ እስከ አሁን ምን ያህል እንደሆነ ካለመገለጹም በላይ የገንዘቡ ወደ ካዝና መግባትና ለሙስና የተጋለጠው አሰራር በሀገሪቱ የገበያ ግሽበት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ብዙዎች እንደሚስማሙበት አዲስ አበባ የሚገኘው ዘጋቢያችን ካሰባሰበው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ