ባህላችን በፖለቲካችን ያለው ገጽታ አዎንታዊ ወይንስ አሉታዊ?

Ethiopia Zare (አርብ ሰኔ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. June 24, 2011):- በካናዳዋ ዋናየንግድ ከተማ ቶሮንቶ የተቋቋመው አድባር የክርክር ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያዘጋጀው መድረክ ጋዜጠኛና የህግ ተማሪ የሆነው ዳንኤል ጥላሁንና የሲቪል ኢንጂኒዬሪንግ ምሩቅ የሆነው ወጣት ኪሩቤል ፍሬው በሚያካሂዱት ክርክር እንደሚጀመር ተገለጸ። 

 

ክርክሩ "የኢትዮጵያዊያን ባህል በፖለቲካው እንቅስቃሴ ላይ ያለው አስተዋጽኦ አዎንታዊ ነው ወይንስ አሉታዊ?" የሚል ሲሆን ዳንኤል ጥላሁን ባህላችን በፖለቲካው ላይ አዎንታዊ (የሚጠቅም) ገጽታ አለው በማለት እንደሚከራከርና አቶ ኪሩቤል ደግሞ ባህላችን ለሀገራችን ፖለቲካ ያለው አስተዋጽኦ አሉታዊ (ጎጂ) ነው ሲሉ እንደሚከራከሩ ለማወቅ ተችሏል።

 

ወጣቶቹ ምሁራን በመከራከሪያው ላይ የራሳቸውን ጥናትና ምርምር አድርገው ጭብጥ ያስይዛሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን ይህ አይነት መድረክ ለሀገሪቱ የፖለቲካ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትና ጤናማ የሆነ የውይይት ባህል እንዲዳብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል።

 

ይሄው በካናዳዋ ከተማ ዛሬ አርብ ጁን 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ከ7pm ጀምሮ በሂሩት ምግብ ቤት 2050 Danforth Ave ላይ የሚካሄደው የውይይት መድረክ በአድባር የክርክር ክበብ አዘጋጅነት የሚስተናገድ ሲሆን ለወደፊት በየጊዜው የዚህ አይነት ውይይቶችን በማዘጋጀት በተከታታይ ከተለያዩ ቦታዎች ምሁራንንና ልዩልዩ ግለሰቦችን በማሳተፍ በቀጣይ ለመስራት ሰፊ እቅዶችን የያዘ መሆኑን እና በሌሎች ቦታዎችም ይህንን አይነት የክርክር መድረክ መስፋፋት እንደሚገባ ከአዘጋጆቹ አንዱ ወጣት ዲሜጥሮስ ብርቁ በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገልጿል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ