አንድ ነዋሪ ድልድይ ውስጥ ራሱን ወርውሯል ሁለቱ በጅብ ተበልተዋል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ.ም. June 30, 2011):-  ለቡኤርቱ በተባለ ሰፈር ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ የተገነቡ 1027 ቤቶች መፍረሳቸውንና ከቤቶቹ ባለቤቶች አራቱ ህይወታቸውን ማጥፋታቸውን የአዲስ አበባ ምንጮቻችን አስታወቁ።

 

ላለፉት ዘጠኝ አመታት የውሃና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማግኘት ከቀበሌው መስተዳድር የድጋፍ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው የሚናገሩት የቤቶቹ ባለቤቶች ከዘጠኝ አመታት በኋላ "ሕገ ወጥ" ናችሁ ተብለው ቤቶቹ ያለምንም ማስጠንቀቂያ መፍረሳቸውን ገልጸዋል።

 

ጊዜው ክረምት በመሆኑ ነዋሪዎቹ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውንና ለበሽታ መዳረጋቸውን የአይን ምስክሮች ከመናገራቸውም በላይበድንገት የመኖሪያ ቤቶቹን መፍረስ የሰማ አንድ ግለሰብ ራሱን ድልድይ ውስጥ በመወርወር ህይወቱን ከማጣቱም በላይ ሁለት ሰዎች ደግሞ በላስቲክ ቤት ውስጥ በመኖር ላይ እያሉ በጅብ ተበልተው እንደሞቱ ለመረዳት ተችሏል።

በ1994 ዓ.ም ጀምሮ ቤቶቹ ሲገነቡ የቀበሌው መስተዳድር ድጋፍ ከማድረግ ውጭ ህገ ወጥ ናችሁ የሚል ምንም አይነት ክልከላ እንዳላደረገባቸው የሚናገሩት ነዋሪዎች ቤቶቹ ባላሰብነው ሰዓት ልጆቻችንንና ቤተሰባችንን በላስቲክ ቤት ለማስጠለል ተገደናል ሲሉ ያማርራሉ። ከመስተዳድር ጽኢ/ቤቱ የተሰጠ ምንም አይነት ምላሽ ባይኖርም ቦታዎቹ ለባለሀብቶች (ኢንቨስተሮች) መሰጠታቸው ታውቋል።

 

ቀደም ሲል በሐዋሳ እና በመቀሌ 2700 ቤቶች ፈርሰው እንደነበርና ባለፉት አምስት ወራት ባቻ  በአጠቃላይ 3727 ቤቶች የፈረሱ ሲሆን ከአስር ሺህ በላይ ነዋሪዎች ያለመጠለያ ቀርተዋል። 

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ