የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ያዘጋጀው መሪያው አመታዊ ፌስቲቫሌ አርብ ጁሊይ 1 ቀን በዋሽንግተን ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ።

 


አያሌ ኢትዮጵያዊያን በጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ፡ አርት የተገኙት ከዝግጅቱ ከመጀመሩ ቀደም ሲሆን፡ ሶስት ቀናት የሚካሄደው ይህ ፌስቲቫል የተከፈተው፡ መክብብና አምሳሌ የተሰኙ ኢትዮጵያዊያን ሰዓሉያን ባቀረቧቸው አስደናቂና ማራኪ የስእል ስራዎች፡ እንዱሁም በአርበኞች ፎቶግራፎች ነው።


በመቀጠልም፡ በጆርጅ ታውን ዩኒቨርስቲ የአርት ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር ክሉፎርድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። እንዱሁም የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ ሊቀመንበር አቶ ሼክስፒር ፈይሳም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አሰምተው፡ ረጅም ግዜ ከኢትዮጵያዊያን አይን ተሰውራ የቆየችውና የዚህ ፌስቲቫሌ የክብር እንግዳ የቀድሞዋ የፖቲካ እስረኛ / ብርቱካን ሚደቅሳ በመክፈቻው ዝግጅት ወደ አዲራሹ መግባቷ፡ በተነገረ ግዜ ከፍተኛና የማያቋርጥ ጭብጨባ ተሰምቷል።


የመጻህፍት ፍርሚያ፡ የግጥም ንባቦች፡ የታሪክ ማስታወሻዎችና የሙዚቃ ቅምሻዎች በታዋቂ ገጣምያን የቀረቡ ሲሆን፡ አርቲስት ማርታ ቀጸላ፣ አርቲስት መኮንን፣ ኢትዮጵያዊው የአምአቀፍ ኦልምፒክ ኮሚቴ የቀድሞ ስልጣንናየፒያሳ ልጅ’ የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ፡ አቶ ፍቅሩ ኪዲኔም አጭር ንግግር አድርገዋል። ዝግጅቱን መከታተል የመጣው ሰው ከአዲራሹ ጋር መመጣጠኑ የተነሳ፡ ብዙ ሰዎች ከውጭ እንዲቆሙ የተገደደ ሲሆን፡ ይሄንን የተመከተውና በዚህ ዝግጅት የተሰተው የጥበብ ሙያና ጋዜጠኛ አበበ ው፡ይኼ ዝግጅት በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥል፡ እንደውም አንድ ዋና መንገድ አስዘግተን የኢትዮጵያ ቀን መከበር በትብሏል።


በዚህ የመክፈቻ ዝግጅት ላይ ብዙ ኢትዮጵያዊነትን ያስታወሱ ስሜት ቀስቃሽ ስራዎች ቀርበዋል።


የፌስቲቫሌ ዝግጅቱ  ቅዲሜ ጁሊይ 2 የሚቀጥል ሲሆን፡ ጠዋቱ 9 ሰዓት የእግር ኳስ ጨዋታዎች  ከአትላንታ፣  ከቨርጂኒያ ከባልቲሞርና ከዲሲ በተውጣጡ ቡድኖች ይካሄዳል።

 

 

ከሰዓት በኋላ የቡና ስነስርአት፣ የላጆች አምባ ዝግጅት፣ እንዱሁም በዋንኛነት የቅኝት የባህል ሙዚቃ ቡድን ባህላዊ የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባል። የመካከኛና አጭር ርቀት የሩጫ ውድድርም ይካሄዲል። ይኸው የእግር ኳስ ጨዋታውና የሩጫ ውድድሩ እሁድ ትም ቀጥሎ ይውላል።

 

እሁድ ጁሊይ 3 ቀንታዋቂዎቹ  ድምጻዊያን ብርሃ ተዘራ፡ አበባ ኝ፡ እና መስፍን ዘበርጋ በሚገኙበት  የሙዚቃ ኮንሰርት ይዘጋል።

 

በሁ ቀናት ዝግጅት ነጻ የመኪና ማቆሚያና፡ እግረኞችም ከፎጊ ቦተም   ስቴዱየሙ የሚያመላልስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንተሰናዳ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል። የዝግጅቱን እየተከታተልን እንዘግባለን።


የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ድርጅት በሰሜን አሜሪካ፡ የኢትዮጵያዊነትን ውርስ ማስጠበቅና ኢትዮጵያዊነትን መጠበቅ የተቋቋመ መንግስታዊ ያሌሆንና ትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው።

 

አርብ ጁሊይ 1 2011 .. ዋሽንግተን ዱሲ፡ ተክሚካኤሌ አበበ

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ