Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2011 .. July 3 , 2011):- አርብ፡ ጁላይ 1 ቀን በዋሽንግተን ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አመታዊ ፌስቲቫል  በሁለተኛው ቀን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሎ ውሏል። ዛሬ እሁድ ፍጻሜ ይሆናል።

 

በጠዋቱ ዝግጅት ከእግር ኳስ ጨዋታው ጎን ለጎን፡ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔንና / ዳንኤል ክንዴን ያሳተፈ አስደሳች ውይይይት ተካሄዷል። በተለይ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ስለኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ከጉግስና ገና ጨዋታ እስከ ቅርብ ግዜ ታሪኩ፡ እያዋዙና ተሰብሳቢውን እያዝናኑ ተናግረዋል። በሩጫ ውድድሩ፡ ወጣት ቤተልሄል ከቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ያሸነፈች ሲሆን፡ በእግር ኳሱም እንዲሁ ለዛሬው ውድድር ያለፉት ቡድኖች ታውቀዋል። / ብርቱካን ሚደቅሳ፡ ወደ መድረክ ወጥታ ለህዝቡ ሰላምታ ሰጥታለች።

 

የፌስቲቫል ዝግጅቱ ዛሬ እሁድ ጁላይ 3 የሚዘጋ ሲሆን፡ በመዚጊያው ስነስረአት ላይ / ብርቱካን ሚደቅሳ የተዘጋጀላት ሽልማት ይበረከትላታል። እንዲሁም የመጀመሪያዋን የነጻነት ንግግር ታደርጋለች። ከዚያ ቀደም ብሎ ግን፡ ጠዋት / ብርቱካንና ሌሎች አገር ወዳድ ሴቶች የቁርስ መርሀ-ግብር አላቸው። የአጭር ርቀት ሩጫ ውድድር ማጠቃለያና የእግር ኳስ ጨዋታው ዋንጫ ውድድር ከጠዋቱ 9 ሰዓት ጀምሮ ይደረጋል።

 

የልጆች አምባ ዝግጅት ቀኑን ሙሉ የሚቀጥል ሲሆን፡ የቅኝት የባህል ሙዚቃ ቡድን ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን፡ የአቢሲኒያ ተወዛዋዦች፡ በመጨረሻም ታዋቂዎቹ ድምጻዊያን ብርሀኑ ተዘራ፡ አበባ ደሳለኝ፡ እና መስፍን ዘበርጋ የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ። ዛሬም ነጻ የመኪና ማቆሚያ እንዳለና፡ ለእግረኞችም ከፎጊ ቦተም ድረስ ወደ ስቴዲየሙ የሚያመላልስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተሰናዳ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል። የዝግጅቱን የመጨረሻ ቀን ሂደት በሰፊው እንዘግባለን።

 

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ድርጅት በሰሜን አሜሪካ፡ የኢትዮጵያዊነትን ውርስ ለማስጠበቅና ኢትዮጵያዊነትን ለመጠበቅ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆንና ለትርፍ ያልተቋቋመ፡ ድርጅት ነው።

 

እሁድ ጁላይ 3 2011 .. ዋሽንግተን ዲሲ፡ ተክለሚካኤል አበበ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ