‘ኢትዮጵያ የነጻነት ሀገር አይደለችም፤ የፍትህ አገር አይደለችም’

Ethiopia Zare ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2003 ዓ.ም. July 5, 2011:- ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የኢትዮጵያዊያን ውርስና ቅርስ ማህበር በዋሽንግተን ዲሲ ባዘጋጀው ፌስቲቫል በህዝብ ፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር አደረገች። የቪድዮ መልእክታ ተሰራጭቷል።

 

ወ/ት ብርቱካን ከእስር ከተፈታች በኋላ ከአጫጭር የምስጋና መልእክቶች ውጭ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥባ መቆየቷ የሚታወቅ ሲሆን የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ባዘጋጀው ፌስቲቫል ባደረገችው ንግግር በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በእስር ላይ በነበረች ጊዜ ያደረጉላትን ሙሉ ትብብር አመስግና “ኢትዮጵያ በእውነት ደስታ የምናደርግላት ሀገር ናት?፤ የምናወድሳትስ ሀገር ናት?” በማለት ጥያቄ በማቅረብ ንግግራን የጀመረች ሲሆን “ኢትዮጵያ የነጻነት ሀገር አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የፍትህ ሀገር አይደለችም በማለት ንግግሯን በመቀጠል  ‘በአንድነት እንቁም አንድነታችን ሁሉንም የሚያቅፍ ይሁን” በማለት ንግግሯን አጠቃላለች።

 

ወ/ት ብርቱካን “ዛሬም ስለ ሀገሬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ህልም አልማለሁ። አጠንክሬ ህልም አልማለሁ” የሚል ተስፋ አዘለ ንግግር እንዳደረገች ታውቃል። (የወ/ት ብርቱካንን ሙሉ ንግግር ይህንን በመጫን ይመልከቱ)  

 

 

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ