የምስራቅ ኢትዮጵያ አስከፊ ረሃብ አሳሳቢ ሆኗል
ሊያነቡት የሚገባ ልዩ ዘገባ - ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን
ረሃብ ጊዜ አይሰጥም ከሚለው መራራ ቃል ጋር ያደመው “ጆፌ አሞራ” አርዶ የጣለለትን የሰው ልጅ መልሶ ሊበላው የሞት ደወልን በሰው ልጆች አጠገብ ቆሞ በማሰማት ላይ ነው።ይህ አሰቃቂ የረሃብ እልቂት የሰው ልጆችን መፈጠር የሚአስተላ ሆኗል። አይኖች በእንባ ተሞልተው ሀዘኑን ለመግለጽ አይበቃቸውም። አንጀት እንደ አንዳች ነገር እየዘለለ ይፈርጣል።የቁጭትና የእልህ ሲቃ ሁለመናን እያቃጠለ ወደ እብድነት ይለውጣል። ይህንን የረሃብ ፍርጃ ካየው በስተቀር የሰማው ሊያምነው አይችልም። ቢችልም በአይኑ እንዳየው ሰው የሀዘብ ብትር ውስጡን አይቀጠቅጠው ይሆናል።
ለማንኛውም ይህንን የመሰለ የጠኔና የስቃይ ድምጽ ሰሞኑን በተዘዋወርኩባቸው የምስራቅ ኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ውስጥ ከፍ ብሎ ይሰማል። ሰሚን የሚማጸነው የረሃብተኛ ወገኖቻችን የሲቃ ድምጽ ፈጣን ምላሽን ይሻል በማለት በአሳዛኝ አተራረኩና በቃላት አመራረጡ ወትሮም ቢሆን የማደንቀው የአርባ ምንጩ ተወላጅ ጓደኛየ ነው። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሾፌር በመሆን ለረዥም ጊዜ አገልግሏል። አሁን ደግሞ በዚያው ክልል በኣለም ምግብ ፕሮግራም ሰራተኛ ሆኖ እያገለገለ ይገናል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ባለስልጣንና የአሜሪካ መንግስት ምክትል አስተዳደር በምሰራቅ ኢትዮጵአ ክልል ተዘዋውረው አስደንጋጩን የረሃብ አደጋ ተመልክተዋል።
ረሃቡን አሳሳቢነት በዚሁ ሰሞን በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። ኦክስፋም የተባለው ዓለም ዓቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት በበኩሉ በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ድርቅ የሚአስከትለው ረሃብ በአካባቢው 60ዓመታት በፊት ከታው አሰቃቂ ክስተት ጋር ይመሳሰላል።ሲል አደገናነቱን ገለጸው በዚሁ ሰሞን ነው። ሁሉም የኢትዮጵያ ምስራቃዊ ክልል በሱማሌ አካባቢ አስከፊው የረሃብ ደመና በሰው ልጆች ላይ እየወረደ መሆኑን “እጅግ በጣም አሳሳቢና አደገኛ” ሲሉ ገልጠውታል።
ጠ/ሚ መለስ ይህንኑ የረሃብ አደጋ እንዳለፈው በቁትር አስበው ለመደበቅ አልደፈሩም። ከአራት ዓመታት በፊት 11 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ለረሃብ አደጋ ተጋልተዋል የሚለውን የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መግለቻ “ቁጥሩ በታም የተጋነነ ነው። ይህንን አይነት ጩኸት የሚያሰሙ “አለን ሚስቶች” ሲሉ መውቀሳቸውን የሚያስታውሱት የረድኤት ድርጅቶቹ ባለስልጣናት የረሃብ አደጋው አስከፊ እንደሚሆን ቅድመ ትንበያው በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩልመገለጡን ጠቅሰው ደግመን ግን ማሳሰብ አልፈለግንም ካሉ በኋላ ከአራት አመታት በፊት ስለ ረሃቡ ደጋግመን በማሳሰባችን በጠ/ሚ/ር መለስ ተዘልፈናል። ዳግመኛ ከሞራል ባፈነገጠ የነገር ጅራፍ ሕሊናችን እንዲገረፍ አልፈቀድንምና ይህንን አሳዛኝ የረሃብ አደጋ ደጋግመን ለመግለጽ አልደፈርንም። ሲሊ የገቡበትን የህሊና እዳ በቃላት ሊወጡት ሞክረዋል።
ጠ/ሚ/ር መለስ በበኩላቸው አሁንም በኢትዮጵያ በረሃብ ምክንያት ሰው እየሞተ አይደለም። ለጋሾች ከገቡት ቃል ግማሹን ያህል እንኳን ባለመስጠታቸው አደጋውን ከፍ አድርጎታል። በአቅማችን ስርኢ ያለውን ሁሉ ተጠቅመን የሰውን ህይወት ለማትረፍ እሰራን ነው። ሲሉ መከራከሪአ አቀርባሉ። ተመልካቾች ስር የሰደደውን ረሃብ ካለፉት ሁለት ዓመታት ዝናብ እጥረት ጋር ተያይዞ በዚህ ዓመት አስከፊ እንደሚሆን ለመገመት አያስቸግርም፤ ችግሩን ሁሉ ለውጭ ለጋሽ ድርጅቶች ከማሸከም በፊት መንግስት የመከላከል ግዴታውን ለመወጣት ከደርግ፣ ከቀዳማዊ ኃኢለ ስላሴ መንግስታትና ከራሱም ተሞክሮ አንጻር በቂ ልምድ ኤአንሰውም ነበር ሲሉ የተጠያቂነቱን እዳ መንግስት በራሱ ድክመት ልክ ሊሰከመው ይገባል ይላሉ።
“ረሃብ አድፍጦ የሚመጣ የጨለማ ውስጥ አውሬ” እንዳልሆነ የሚናገሩት አንድ የዓለም ዓቀፍ ረድኤት ድርጅት ባለስልጣን ለድርቁ መከሰት ከበቂ በላይ ምክንያቶች እንደነበሩ ይተቅሳሉ። ሆኖም በእነዚህ ላይ ተመስርቶ የመከላከል ተግባር አለመከናወኑ የተጤአቂነቱን እዳ ምንኛችንም የእና አይደለም ብለን የትም ልንወረውረው አንችልም ሲሉ ዝምታውን ኮንነዋል።
የአሜሪካ አምባሳደርን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ባለስልጣንና የአሜሪካ መንግስት ምክትል አስተዳደር አካባቢውን ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ይህንን አስከፊና አሳዛኝ የድርቅ አደጋ ምናኛውም ወገን ችላ ሊለው አይገባም ሲሉ አሳስበዋል።ሁሉንም በሚያስማማውና ሰሞኑን ይፋ በሆነው መረጃ መሰረት 4 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የረሀብ አደጋው ሰለባ እንደሆኑ ታምኖበታል።
የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ላቀረብኩት የእርዳታ ጥሪ ምላሽ ተነፍጎኛል በሚል በዚህ ሰሞን በድጋሚ የድረሱልም ጥሪ ማቅረቡ ተመልክቷል። ከግብርና ሚኒስትር በወጣው መረጃ መሰረት ደግሞ የበልጉ ዝንብ በተፈለገው ጊዜ ባለመምጣቱ ድርቁ ከምስራቅ ክልል በተጨማሪ በኦሮሚያ፣ በአፋርና በአማራ ክልሎችም መከሰቱን ጠቅሶ በእጃችን ከሚገኘው የምግብ እህል ክምችት ለተጎጅው ሕዝብ እያደልን ነው ሲል ያስረዳል።
የዘንድሮው ረሃብ የከፋ ከመሆኑም በላይ መላውን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ያጠቃ መሆኑ የአንደናው አገር ህዝብ ተጎጅ ወደ ሌላኛው አገር ተዛውሮ ነፍሱን ምቆየት እንዳይችል ደንቃራው አይሎበታል የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች ከመንግስት አልባዋ ሶማሌ በርካታ ስደተኞች ወደ ኬንያ ያቀኑ ሲሆን በአካባቢው ካለው ፖለቲካ ጦስ ጋር ተደማምሮ ስደተኞች መበራከት እርዳታ ለጋሽ ሀገሮችንና ድርጅቶችን ፋታ የነሳ አጋታሚ ላይ እንደታላቸው ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።
ዘግይቶ የተሰማው የረሃብተኞች ጥሪ አስቸኳይ እርዳታ ካልተደረገለት በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ህይወት እንደሚቀተፍ የሚናገሩት ታዛቢዎች በተለይ የአፍሪካ ቀንድ መንግስታት የፖለቲካ ቀውስ እንዳይሰፋባቸው ችግሩን ችላ ማለታቸውና በለጋሽ አገሮች የሚታየው የፋይናንስ ቀውስ በረሃብ ለሚረግፉ ወገኖች በመፍትሄነት ይደርሱላቸው ይሆን? ከሚለው ጥአቄ ጋር ተዳምሮ በአካባቢው የሚፈጠረው ሰብአዊ ቀውስ የዓለሙን ማህበረሰብ ሁሉ አንገት የሚያስደፋ ሊሆን እንደሚችል ፍራቻቸውን አክለዋል።
ልቅ የሆነው ሙስና ሕግ የለው ጎበዝ ማጣቱና የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታው በጥቂት መሪዎች ዳር መድረስ እአቃተው ባለበት በዚህ ወቅት ለጋሽ የሆኑ የበለጸጉ ሀገሮች የረሃቡን መንስኤና የመከላከል አቅም ማነሱን በተለመከተ “እንዴት?” ብለው ከስሩ የሚመረምሩበት አጋጣሚ ላይ እንደሚያደርሳቸው የሚናገሩት የቀንዱ የፖለቲካ ተንታኞች ከእንግዲህ የአፍሪካ ሀገራት በሚደርስባቸው ማናቸውም ግፍና በደል የበለጸጉት አገሮች በአፍሪካ ውስጥ በረጅሙ የዘረጉት እጅ ያደረሰውን ቀውስ ሁሉ ለመመዘን ሚቸገሩ እንዳልሆነም አስምረውበታል። አያይዘውም ድርቅ ቤትኛውም አገር ኢከሰታል። ለዚህ አደጋ ጊዜ የሚሆን የመጠባበቂአ እህል ማከማቸትና መጪውን አደጋ ለመከላከለል የሚያስችለው ዝግጅት እንደየአገራቱ መንግስታት ብቃትና ቁርጠኝነት የሚለካ ነው ይላሉ።



