Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 26 ቀን 2003 ዓ.ም August 3, 2011):- በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የብጹእ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ክቡር ሥጋ የሚያርፍበት ቦታ ለማዘጋጀት ባወጣው እቅድ መሰረት በስማቸው በተሰየመውና ቴክሳስ - ሂውስተን በተመሰረተው ገዳም ለማሳረፍ ያደረጋቸው ሙከራዎች ጊዜ በመውሰዱ ለጊዜው ብጹእነታቸው ብርታት ከእዳ ነጻ አድርገው በሲያትል ከተማ ባቋቋሙት መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቴድራል የቀብር ስነስርአታቸው እንዲፈጸም ወሰነ።

 

ብጽዕ አቡነ ዜና በስደት ኬንያና ሰሜን አሜሪካ በቆዩባቸው ጊዜያት በስደት የተጎሳቆሉ ዜጎችንና ምእመናንን በመሰብሰብ አባታዊ ምክርን በመስጠት እና በማበረታታት እንዲሁም በርካታ የእግዚአብሔር ቤቶች እንዲገነቡና ህዝበ ክርስቲያን እንዲሰባሰቡ በማድረግ ህይወታቸውን በሙሉ ያሳለፉ መሆኑ ይታወቃል።

 

በውጭ ሀገር በስደት የሚገኘውና ህጋዊው ሲኖዶስ የብጽዕነታቸው ስርአተ መቃብር እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በያዝነው ወር ኦገስት 27/2011 ዓ.ም በሲአትል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈጸም ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል። (ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ