Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2003 ዓ.ምAugust 16)  የቀድሞ የሕወሀት መስራችና የነጻነት ታጋዩ ዲባቶ አረጋዊ በርሄ በመጪው ቅዳሜ፡ ኦገስት 20 በካናዳ ዋና ከተማ፡ ኦታዋ ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ከኦታዋ የሚተላለፈው የኢትዮጵያ ሬድዮ ዘገበ።

 

ሬድዮው በኦታዋ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የበተኑትን የስብሰባ ጥሪ ወረቀት ምንጭ አድርጎ እንደጠቀሰው፡ ዲባቶ አረጋዊ በርሄ በዚህ ሳምንት መካከል ወደ ኦታዋ የሚገቡ ሲሆን፡ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ 211 ብሮንሰን ጎዳና ላይ በሚገኘው በብሮንሰን ማእከል፡ በኦታዋና አካባቢዋ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ታውቋል።   http://www.facebook.com/pages/Radio-Ethiopia-in-Ottawa/151896154878712

 

በሌላ ዜና፡ ባለፈው ሕወሀት/ኢህአዴግ 99.6 ከመቶ ባሸነፈበት 2010 “ድንቄም ምርጫ፡በአድዋ ወረዳ የቀድሞ አለቃቸውን አቶ መለስ ዜናዊን ተፎካክረው የተወዳደሩት ሌላዋ የቀድሞ የህወሀት ታጋይና ማእከላዊ ምክርቤት አባል፡ የአሁኑ አረና መስራችና ከፍተኛ አመራር፡ / አረጋሽ አዳነ፡ በምርጫው ሰሞን የገንዘብ ልገሳ ላደረጉላቸው ኢትዮጵያዊያን ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ላለፉት ትቂት ሳምንታት ለህክምና አሜሪካን አገር የሚገኙት / አረጋሽ አዳነ፡ በተለይም በዚህ ዜና ዘጋቢ (እኔ ተክሌ ነኝ) አስተባባሪነት በቫንኩቨርና ሲያትል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለምርጫው እንዲያግዛቸው የላኩላቸውን 14 ሺህ ብር አስመልክተው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

 

/ አረጋሽ አዳነም፡ ከህወሀት ባለስልጣናት ከፍተኛ ማስፈራሪያና ጫና ቢኖርባቸውም፡ ወደኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊት በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያዊያን ጋር በአገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የዚህን ዜና ዘጋቢ ጨምሮ፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች፡ ህወሀትን ለዚህ ደረጃ ያበቁ እንደ አቶ ስየ፡ / አረጋሽና አቶ አረጋዊ አሉ ሰዎች፡ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ሳይርቁ ሕወሀትን ለድል ባበቁበት መንገድ እንዲያወርዱት ብዙ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል። በተለይም የትግራይ ህዝብና የተቀረው ኢትዮጵያዊ ህዘብ መካከል ልዩነትን በማስፋት ስልጣኑን እያጠናከረ ያለው ሕወሀት/ኢህአዴግን ለማዳከምና ለመጣል፡ የትግራይ ህዝብ ተሳትፎ ወሳን እንደመሆኑ መጠን፡ እነ / አረጋሽና አቶ ስዬ እንዲሁም ዲባቶ አረጋዊ በርሄ፤ በትግራይና በተቀረው ኢትዮጵያ መካከል፡ በሕወሀት/ኢህአዴግ የተሸረሸረውን መተማመን በመገንባት ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ አስተያየት ሰጥተዋል።

 

የኦታዋውን ስብሰባ ሙሉ ዘገባ በምስልና በጽሁፍ እንደምናቀርብላችሁ ቃል እንገባለን። በዚህ ወር ውስጥ በኦታዋ ህዝባዊ ስብሰባ ሲካሄድ ይሄ ሁለተኛው ነው። በኦታዋ በቅርቡ በተካሄደ ስብሰባ፡ ንግግሩ ቪዲዮ ካሜራ እንዳይቀረጽ የተከለከለ ሲሆን፡ http://ethiopiazare.com/the-news/latest/1-latest-news/1818-lij-tekle እንኩዋንስ ቪዲዮ ካሜራ ታንክና መድፍም ፊትም የቆሙትና ንብረቴ ይወረሳል ብለው የማይፈሩት አረጋዊ በርሄ ንግግራቸው በቪዲዮ እንዳይቀረጽ እንደማይከለክሉ እንጠብቃለን። በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ዜና ትንታኔ ለመስማት ዘወትር እሁድ ከሰዓት በኋላ 2 ሰዓት ጀምሮ የሚተላለፈውን የኢትዮጵያ ሬድዮ በኦታዋ፡ http://chuo.fm/  ላይ በቀጥታ እንድታዳምጡ እንጋብዛለን።

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ