አድባር፡ ሶስተኛውን ክርክር በቶሮንቶ አዘጋጅቷል
Ethiopia Zare (አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2003 ዓ.ም August 26 2011) :- ባለፈው ግንቦት የተቋቋመውና መቀመጫው በቶሮንቶ የሆነው “አድባር የክርክር ማህበር” ሶስተኛውን የክርክር ዝግጅት በያዝነው ሳምንት፡ አርብ፡ ኦገስት 26 ከሰዓት በኋላ፡ ከ5 ሰዓት ጀምሮ፡ በሂሩት የሀበሻ ሬስቶራንት እንደሚያደርግ በላከው አጭር መግለጫ አስታወቀ።
አድባር የክርክር ማህበር፡ ከዚህ ቀደም፡ በኢትዮጵያ ባህልና ባህላችን በፖለቲካችን ላይ ባለው ተጽእኖ፡ እንዲሁም በትዳር ግንኙነትና ጉዳዮች ላይ፡ የተሳካ ውይይት ያደረገ ሲሆን፡ በዚሕኛው ሶስተኛው ክርክር ላይ፡ ወጣት ዲሜጥሮስ ብርቁና፡ ተክሌ አበበ መርጋ፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አሁን ድረስ አከራካሪ በሆነው፡ በፖለቲካዊ ሀሳብና በብሔር የተደራጁ የፖለቲካ ሃይሎች በሚያቀነቅኑት የ"ቅኝ ግዛት" አስተሳሰብ ላይ ይከራከራሉ።
አድራሻ-2050 ዳንፎርዝ አቬኒዮ ፤ቶሮንቶ) በቶሮንቶ አና አካባቢዉ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እንድትገኙ ጋብዘዋል።
ክርክሩ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክና በቃሌ፡ እንዲሁም በሌሎች የፓልቶክ ክፍሎችም ስለሚተላለፍ፡ በፓልቶኮች እንድትከታተሉ ግብዣ ቀርቧል። አድባር ከዚህ በፊት ያደረጋቸውን ክርክሮች ዝርዝር ዘገባ፡ እዚህ ላይ ይመልከቱ። http://www.facebook.com/groups/218520534848685/
ወጣት ተክሌ፡ ከቶሮንቶ፡ ካናዳ፤ ነሀሴ፡ 2011



