Ethiopia Zare (ማክሰኞ መስከረም 30 ቀን 2004 ዓ.ም. October 11, 2011)፦ የካናዳ መንግስት መቀመጫ በሆነችው ኦታዋ ዛሬ ምክሰኞ ኦክቶበር 11 ቀን 2011 ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ከስፍራው የደረሰን ዘገባ አስረዳ።

 

 

ይሄው በኢትዮ - ካናዲያን ፍረም ለዲሞክራሲ በመባል በሚታወቀውና በርካታ ኢትዮጵያዊያንን ባሳተፈ ተቋም የተዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ በተለይ በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ በሚገኙ የሰላማዊ ታጋዮችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች ላይ በመጥፎነቱ የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት በሽብርተኝነት ስም እያደረሰ ያለውን እስራት ለመቃወም እንደሆነ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል።

 

ተቋሙ ባለ ስምንት ነጥብ በያዘ መግለጫው በተለይ ላለፉት አስርት አመታት በሀገሪቱ እየተፈጸመ ያለውን ዘረኛ አገዛዝ እንደሚቃወም ገልጾ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በመካከላቸው ያለውን አነስተኛ ልዩነቶች አቻችለው በአንድነት እንዲነሱ አሳስቧል።

 

በተለያዩ አለማት የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ሀገርንና ህዝብን ለማዳን እንነሳ የሚለው ይሄው መግለጫ “ፋሽስት” ያለውን አገዛዝ አስወግዶ ነጻነት፤ ዲሞክራሲና የህግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት እንነሳ ሲል ጥሪውን አስተላልፏል።

 

በኦታዋ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ መረከረሰኞ ኦክቶበር 11 ቀን 2011 ከ11፡30 – 1፡00 በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ይካሄዳል።

 

(ሙሉ የመግለጫውን ለማንበብ ይህንን ይጫ)

 

(ማስታወቂያውን ለማየት ይህንን ይጫኑ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ