አያሌ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት ተገኝተው ነበር

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ.ም. December 6, 2011)፦ ከማል አቡበከር ይባላል። የአገሩ ጉዳይ የሚያንገበግበው ጎልማሳ ነው። በእለቱ የቤቱን እቃ ለማጓጓዝ የጭነት መኪና ለስድስት ሰዓት ያህል ቢከራይም፡ የየኔሰው ገብሬ መታሰቢያ እንደሚደረግ ስነግረው፡ መኪናውን ከመንገድ ጥግ አቁሞ ወደ ካናዳ ፓርላማ ለመጓዝ ሰከንድም አልፈጀበትም። “አረ ትኬት እንዳይሰጡህ” ቢባልም “እንኩዋን ትኬት መስጠት፡ ጎትተውም ይውሰዱት ከፈለጉ” ብሎ ወደ ሻማ ማብራቱ አቀና። እሁድ፡ ዲሴምበር 4፡ 2011 ዓ.ም፡ ከሰኣት በኋላ።

 

በካናዳ መንግስት መቀመጫ፡ ኦታዋ በካናዳ ፓርላሜንት ፊትለፊት በተካሄደ የሻማ ማብራት ላይ፡ በቅርቡ ራሱን ለነጻነትና ለፍትህ አሳልፎ የሰጠው ወጣት የኔሰው ገብሬ ታስቦ ውሏል። በዚህ በኢትዮጵያ ካናዲያውያን መድረክ ለዴሞክራሲና በአካባቢው በሚገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በተጠራ የሻማ መብራት ስነስርአት ላይ፡ ከበቃ፡ ግንቦት ሰባት፡ ኢህአፓና መሰል ድርጅቶች የተወጣጡ ሰዎች ተገኝተዋል። የየኔሰውን መስዋእትነት በተመለከተ የተዘጋጀው መግለጫም ተነቧል።

 

በሻማ ማብራት ስነስርአቱ ላይ በተደረገው ንግግር፡ በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ የሚደረገውን ትግል እንደሚያግዙ ቃል ተገብቶ፡ በሌሎች አካባቢ የሚገኙ ድርጅቶችም ይህንኑ ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ ተደርጓል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ