በዋሽንግተን ዲሲ ወርሀዊ የሻማ መብራት ስነስርአት ተካሄደ!

Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ.ም. January 2, 2011)፦ በ”ማርች ፎር ፍሪደም”ና በሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አስተባባሪነት በየወሩ በአሜሪካን ፕሬዚዳንት መኖሪያ ፊት ለፊት የሚካሄደውና በኢትዮጵያ የታሰሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን የሚያስበው የሻማ ማብራት ስነስርአት በሞቀ ሁኔታ ተካሄደ።

 

በዚህ እነእስክንደር ነጋ ከታሰሩ ወዲህ ለሶስተኛ ግዜ በተካሄደው የሻማ ማብራት ስነስርአት ላይ አያሌ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን፡ የአሜሪካን መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ያለውን ፖሊሲ እንዲቀይር የሚጠይቁና የኢህአዴግ ህወሀት መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን ባስቸኳይ እንዲፈታ የሚያሳስቡ መፈክሮች ተሰምተዋል። በዚህ ከዋይት ሀውስ አጥር ስር በተካሄደ ሰልፍ ላይ ሴቶችና ወጣቶች በብዛት የተገኙ ሲሆን፡ ዝናብና ብርድ ያልበገራቸው ተሰላፊዎቹ በታላቅ ሞራልና መነሳሳት መፈክሮችንና ጣእመ ዜማዎችን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

 

የሰልፉ አስተባባሪ ዶ/ር ካሳ አያሌው፡ ለሰልፉ የተገኙትን ሰዎች አመስግነው፡ በሚቀጥለው ወርም የሻማ ማብራት ስርአቱ እንደሚደረግ ተናግረዋል። በእለቱ፡ የታዋቂው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ፡ እስክንድር ነጋ አክስት፡ የእናቱ የሲስተር በላይነሽ እህት በሰልፉ ላይ ተገኝተው፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለእስክንድርና ለሌሎቹም እስረኞች እንዲጸልይላቸው ጠይቀዋል። የእስክንድር አክስት አክለውም፡ የስዊድን ጋዜጠኞችን 11 አመት ፈረድኩባቸው ያለው ውሸቱንና እኛን ለማስፈራራት፡ እንደሆነና በቅርቡ እንደሚለቃቸውም ተናግረዋል። (ይህንን በመጫን ፎቶግራፍ ይመልከቱ)

 

ታህሳስ፡ 2004፡ ተክሌ፡ ዋሽንግተን ዲሲ፡

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ