የኢትዮጵያ ባንኮች ተቀማጭ ገንዘባቸው በመቀነሱ ትርፋቸውም መቀነሱ ተገለጸ
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ ብሉምበርግ የአክሰስ ካፒታል ሼር ካምፓኒን ጠቅሶ እንደዘገበው በዚህ አመት የኢትዮጲያ ባንኮች ትርፋቸው እየቀነሰ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ህጉ አበዳሪዎች ከመንግስት የዋስትና ሰነድ (ሴኩሪቲ)እንዲገዙ ስለሚጠይቅ መሆኑን ገልጿል።
በሚቀጥሉት አመታት ከሃብት ተመላሽ የሚሆነው 20% የሚጠበቅ ሲሆን ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 30% ጭማሪ አሳይቷል። አክሰስ እንዳለው በጥር 19 በተላካ የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በጠቅላላ ገቢው የወረደ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የማበደር አቅሙ ደካማ መሆኑና የባንኮች የእድገት ድርሻ በመቀነሱ ሃብት በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ ወረቀት ላይ ብቻ የሰፈረ መሆኑን አክሰስ ገልጿል።
የተቀማጭ እድገቱም በዚህ ዓመት ከ20 ወደ 25% ሲቀንስ ከባለፈው ዓመት 30% የቀነሰበት ምክንያት አነስተኛ የገንዘብ አቅርቦትና በባንኮች መካከል ያለው ፉክክር መሆኑን ጨምሮ አስታውቋል። ሚያዚያ ወር ላይ ብሄራዊ ባንክ እንዳስታወቀው ባንኮች ከአጠቃላይ ብድራቸው 27%ቱን የዋስትና ሰነድ መግዛት አለባቸው ይህም ለመሰረተ ልማቱ ፕሮጀክት ያግዛል ብሏል።



