Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ ሁለቱ ባለስልጣናት የታሰሩት እሁድ ከሰዓት የሰላም ስምምነቱን ካፈረሱ በሁዋላ መሆኑን ሶማልላንድ ፕሬስ ዘግቡዋል። የታሰሩት ባለስልጣናት አደን አብድላሂ አወል የሱማሌ ክልል አኩ ሱና ፓርላማ ቡድን መሪ እና አብዱልፈታህ ሀሰን ጃማ የሸበሌ ቫሊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት መሆናቸው ታውቋል

 

የአይን እማኞች እንደገለጡት የኢትዮጲያ ወታደሮች ሁለቱ ቡድኖች ተስማምተው በጋራ አል ሽባብን እንዲዋጉ እየሞከሩ ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች ሀሳቡን ውድቅ በማድረግ እርስ በእርስ የተነሱ ሲሆን የኢትዮጲያ ወታደሮች የውስጥ ችግሮችን ለመዳኘት ከመሰልቸቱ የተነሳ ሊያስሯቸው ተገደዋል። ከከተማ ውጪ በሚገኘው የኢትዮጲያ ወታደሮች ካምፕ አንድ ምሽት ከታሰሩ በሁዋላ የለቀቁዋቸው ሲሆን በቀጣይ የሱማሌ መሪዎች ለህዝቡ ደህንነት በጋራ የማይሰሩ ከሆነ እንደሚያስሩዋቸው ገልጸዋል።

 

በታህሳስ 2004  የኢትዮጲያ ወታደች በልደወይን ከተማን ከአልሽባብ ያስለቀቀ ሲሆን በሱማሌ ሰላም ለማምጣትና የሱማሌን የአስተዳደር ሁኔታ ለመቀየር የሰለቸ ሲሆን ከተማውን ለ አፍሪካ ህብረት ለማስረከብ ወስኗል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ