በኦታዋ ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በግፍ ለታሰሩ አርበኞች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ
ፎረም ኦታዋ ለሰብዓዊ መብትና ለዲሞክራሲ በሚል መጠሪያ የተሰባሰቡ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ እስር ቤት ተጥለው በመማቀቅ ላይ ለሚገኙ አርበኞችና ቤተሰቦቻቸው መርጃ የሚሆን ገንዘብ አሰባስበው ወደ አገር ቤት ላኩ።
የፎረሙ አባላት በእስር ላይ የሚገኙትን አርበኞች ለማስፈታት በኦታዋና አካባቢው የሚገኙትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ግንዛቤ እንዲያገኙ (ሎቢ) በማድረግ ወያኔ ከኢ-ሰብዓዊ ተግባሩ እንዲታቀብ ግፊት እንዲያደርጉ አጠንክረው በማሳሰብ ፤ ጐን ለጐንም የገንዘብ እርዳታውን ተከታታይነት ባለው ሁኔታ እንደሚቀጥሉ ታውቋል።
አያይዘውም ወያኔ በገዛ ህዝቡ ላይ በየጊዜው ከሚወስደው የአፈናና የእመቃ ተቃውሞ ባሻገር ኢትዮጵያን ለመታደግና ሥርዓቱን ለመገርሰስ የሚደረገው ርብርቦሽ ቀዳሚ መሆን እንደሚገባው በማመን ለዚሁ ተግባር ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችው ጋር በመተባበር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።



