ጥሪውን ያቀረቡት አስራ ሁለት በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኀን ናቸው

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዚያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. April 19, 2012)፦ አስራ ሁለት በስደት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኀን በጋራ በመሆን ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 7 ቀን 2004 ዓ.ም. (April 14, 2012) በአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ ላይ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ አስተላልፈዋል።

 

 

መገናኛ ብዙኀኑ ህዝባዊ ጥሪውን ለማቅረብ የጠሩትን ስብሰባ ከ600 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በኢንተርኔት ተከታትለውታል። የጋራ መግለጫቸው ከዚህ በታች ይነበባል።

 

የኢኮኖሚ ማዕቀብ ህዝባዊ ጥሪው የሚከተሉትን ያጠቃልላል፤

 

1. በአሁኑ ወቅት ከዋና አስተዳደሩ ጀምሮ በጠቅላላ በህወሃት አባላት ቁጥጥር ስር የወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ትርፍ ለመለስ ዜናዊና ግብረአበሮቹ እያስገኘላቸው ይገኛል። ይህ ድርጅት ከስሙ በስተቀር ኢትዮጵያዊነት ባህሪይ የሌለው፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አይነት ጥቅም የማያስገኝ ሆኖ ስለተገኘ ይህ ህዝባዊ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ማንኛውም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ አየር መንገዱን እንዳይጠቀም፣

 

2. አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ማንኛውንም አይነት ማህበረሰባዊ ግንኙነት ከወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ጋር ማቆም፣

 

3. ከኢትዮጵያ የሚመጡ ቢራዎች፤ እንጀራና ሌሎችንም ወያኔ የሚቆጣረሯቸው ድርጅቶች የሚያመርቷቸውን ምርቶች አለመጠቀም።

 

ይህን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያን ከህወሃት አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የሚታገሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሁሉ የበኩላቸውን ዝግጅትና ጥረት እንዲያደርጉ እንማጸናለን።

 

የሀይማኖት አባቶች፣ አርቲስቶች፣ ምሁራን፣ ስፖርተኞች፣ ነጋዴዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ማንኛውም ለሀገርና ለህዝብ የሚቆረቆር ኢትዮጵያዊ ይህን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሪ እንዲያስተጋቡልንና ተፈጻሚ ለማድረግ እንዲተባበሩ እንጠይቃለን።

 

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ።

 

- አዲስ ድምጽ ራዲዮ

- ዳላስ የኢትዮጵያ ድምጽ ራዲዮ

- ኢትዮሜዲያ (Ethiomedia.com)

- ኢትዮጵያ ዶት ኦርግ (Ethiopia.org)

- የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የውይይት መድረክ (Ethiopian Current Affairs Discussion Forum)

- ኢትዮጵያን ሪቪው (EthiopianReview.com)

- ሕሊና ራዲዮ

- ኅብር ራዲዮ

- ቃሌ የውይይት መድረክ (Qale Ethiopian Discussion Forum)

- ማኅደረ አንድነት ራዲዮ

- ነፃነት ለኢትዮጵያ ራዲዮ

- ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ