EMF: (ዓርብ ሚያዚያ 19 ቀን 2004 ዓ.ም. April 27, 2012)፦ ከዋናው ፌዴሬሽን ተገንጥሎ ስሙን ESFNA One ብሎ የነበረው የነአያያ እና የነሰብስቤ ቡድን ትላንት እና ዛሬ ዲሲ ላይ ስብሰባ አድርጎ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ በዋና አጀንዳነት ከቀረቡት ጉዳዮች አንዱ የነበረው ባለፈው ሳምንት በቨርጂንያ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ነበር።

 

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ESFNA One እራሱን ከዋናው ፌዴሬሽን ጋር እንዳያገናኝ፤ ብሎም የዋናውን ስፖርት ፌዴሬሽን ስም እንዳይጠቀም ይህንንም በግልጽ እንዲያሳውቅ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠ መሆኑ ይታወሳል። በዚህም መሰረት የድረ-ገጹን ስም http://www.esfnaone.org ባይቀይሩትን በድረ ገጻቸው ላይ፤ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት የሚከተለውን ማስታወቂያ አውጥተዋል።


“Ethiopian Sport Federation in North America One, Inc. has no connection with Ethiopian Sport Federation in North America, Inc. and has not previously sponsored any soccer tournament.”


በዚህም መሰረት ESFNA የሚለውን ስም ከ’ንግዲህ በኋላ አይጠቀሙበትም። በዚያ ምትክ ራሳቸውን ዓሳ ወይም AESA one ብለው ሰይመዋል።


ከዚህ በታች ያለው የፎቶግራፍ ጥንቅር፤ የተገነጠሉት የፌዴሬሽኑ አባላት ስብሰባ ሲያደርጉ፤ የዲሲውን ስቴዲየም ለመጎብኘት ሲሄዱ፤ በባስ ውስጥ ሆነው እና በመጨረሻም ስቴዲየሙ ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ነው።


 

በዋናው የሰሜን አሜሪካ ፌዴሬሽንና የተገነጠሉትን ሰዎች አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔውን ለመስጠት ዛሬ ኤፕሪል 17 ቀን፣ 2012 ዓ.ም. ይሰየማል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ቴዲ አፍሮ በዳላሱ የዋናው ስፖርት ፌዴሬሽን ዝግጅት ላይ የሚገኝ መሆኑ ታውቋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ