"ትእቢተኛ ነገስታት የነበሩት እነ ናቡከደነጾር በጸሎት ተሸንፈዋል" መላከጸሐይ አፈወርቅ

Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. June 17, 2012)በቫንኩቨር-ካናዳ የምትገኘው ጸደንያ ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ ጸሐይ አፈወርቅ በዋልድባ ገዳም አካባቢ እየተፈጸመ ያለውን የእርሻ ቁፋሮ እና በመነኮሳት ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት ለማስቆም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታይ ምእመናን ምህላ እንዲገቡ ጥሪ አስተላለፉ።

 

በዋልድባ አካባቢ በመንግስት እየተፈጸመ ያለውን የእርሻ ቁፋሮ በመቃወም በተለያዩ የአለም ክፍሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቁጣንና ተቃውሞ ቀስቅሶ መሰንበቱ የሚታወቅ ሲሆን በቫንኩቨር ካናዳ የጸደንያ ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን የበላይ አስተዳዳሪ የሆኑት አባ መላከ ጸሐይ አፈወርቅ በመላው አለም የሚገኙ ምእመናን ኃያሉ አግዚያብሔር ትእቢተኛ ነገስታት የነበሩት እነ ናቡከደነጾር ዳንኤልን ባሰቃየበት ወቅት አምላክ በጸሎት እንደታደገው ሁሉ ምእመናን ፊታቸውን ወደ እግዚአብሄር በማዞር ምህላ (ጾም ጸሎት) ይገቡ ዘንድ ጠይቀዋል።

500 ካህናተ ሐሰት የነበሩት አክአብም በጾምና ጸሎት እንደተሸነፈው ሁሉ አሁንም ምእመናን ከሚያደርጉት ተቃውሞ ባሻገር ራሳቸውንና ጊዜያቸውን ወደ እግዚአብሔር በማዞር ለዘመናት ተከብሮና በአምላክ ተጠብቆ የኖረው ገዳም ክብሩን ጠብቆ እንዲኖር ምህላ መግባት ግድ እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።

በቫንኩቨር የምህላ ጾም ጸሎት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የቀጠለ ሲሆን ሌሎች አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትም ፊታቸውን ወደ ልዑል እግዚአብሔር በማዞር ልመናና ጸሎታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀው መፍትሔውም ለአለም መንግስታት ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊያኖች በአንድነት መቆም ሲችሉ እንደሆነ ተገልጿል።

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ