እስክንድር ነጋ 18 ዓመት እስር ተወስኖበታል

አንዷለም አራጌ እድሜ ልክ እስራት ተብሏል

ቁጥር ለመስማት ነበር የሄድነው እሱን ሰምተን ተመልሰናልየእስክንድር ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል

Ethiopia Zare (አርብ ሐምሌ 6 ቀን 2004 .. july 13, 2012)፦ በህወሃት ኢህአዴግ ቁጥጥር ስር የሚገኘውና አሻንጉሊት ዳኞችን በመሰየም የሚታወቀው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ዛሬ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ውሳኔ ሰጠ። አንዷለም አራጌ የእድሜ ልክ ሲፈረድበት ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ የሆነው እስክንድር ነጋ 18 ዓመት ተወስኖበታል።

 

ዛሬ ለውሳኔ የተቀመጠው የከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነአንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ 24 ተከሳሾችን አስመልክቶ የቅጣት ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን የግንቦት 7 አመራር በሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ ነጋና  አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲሁም የኢሳቱን ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ላይ የእድሜ ልክ እስራት ፈርዷል።

 

በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና በሌሎች ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ባልተገኙት ጋዜጠኛ አበበ ገላውና ኦባንግ ሜቶ ላይም የ18 አመት እስራት የወሰነባቸው ሲሆን በሌሎች አምስት ተከሳሾች ላይ የ15 ዓመት ጽኑ እስራት በመፍረድ ዛሬ በልደታ አካባቢ የሚገኘው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ተበትኗል።

 

በስፍራው እንደቀድሞው ሁሉ አምባሳደሮችና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች የተገኙ ሲሆን በርካቶች ሀዘናቸውን የገለጹበት እንደነበርም ለመረዳት ችለናል።

 

የእስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል የዛሬውን የፍርድ ሂደት ከአሁን በፊት የነበረውን የብይን ሂደት ማለትም ጥፋተኛ ናቸው አይደሉም የሚለውን ለመስማት እንደሄደችበት ጊዜ ምንም ቦታ ያልሰጠችው እንደነበር ገልጻ የዛሬውን ቀን “ቁጥር ለመስማት ነበር የሄድነው ቁጥሩን ሰምተን ተመልሰናል” ስትል ከፍርድ ውሳኔው በኋላ በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ አስተያየቷን ገልጻለች።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ