የአክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ የአውስትራሊያ ቆይታ ጠቅላላ ሪፖርት
ላለፉት 8 ዓመታት አገራዊ ፋይዳ ያላቸውንና ለህዝባችን ሁለንተናዊ ነጻነት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ሲንቀሳቀስ የቆየው የሜልበርን ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን ባደረገለት ግብዣ በ 12/08/12 አውስትራሊያ የገባው ተወዳጁና እውቁ የጥበብ ሰው አርቲስት ታማኝ በየነ በአውስትራሊያ 5 የተለያዩ ከተሞች ማለትም በሜልበርን ፤ በሲድኒ፤ በአድላይድ፤ በብሪዝበንና በፐርዝ በተከናወኑ የኢሳት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት ከ 115 ሺህ በላይ ዶላር ማሰባሰብ ችሏል።
አርቲስት ታማኝ የመጀመሪያ ዝግጅቱን AUGUST 11 ሜልበርን ከተማ ላይ እንዲያደርግ በተያዘው እቅድ መሰረት ከዋሽንግቶን በመነሳት ጉዞ ቢጀምርም በበረራ መሰረዝ ምክንያት በታቀደው ቀን ሜልበርን ሊገባ አልቻለም። በመሆኑም የሜልበርኑ ዝግጅት ለተከታይ ሳምንት ሊተላለፍ ግድ ብሏል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)



