አቶ ደሳለኝ ኃይለምሪያም ሊቀመንበር ሲሆኑ በምክትልነት አቶ ደመቀ መኮንን ተመርጠዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2005 .. Sebtember 13, 2012)፦ ለበርካታ ወራት ቁርጡ ባልታወቀ የአመራር ክፍተት ሲታመስ ነበረው ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ለ21 አመታት ሀገሪቱን በሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንትነትና ጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩትን  አቶ መለስ ዜናዊን ቦታ የሚተካ አመራር የመረጠ ሲሆን የድርጅቱ ዋና ሊቀመንበር አቶ ደሳለኝ ኃይለማሪያምን ሲመርጥ  አቶ ደመቀ መኮነንን በምክትል ሊቀመንበርነት ሰየመ።

 

ኢህአዴግ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስን ህልፈት ተከትሎ በበርካታ ውዝግብ ውስጥ የገባውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረግ ሹመት አስመልክቶ በተለያዩ ባለስልጣናቱ አሻሚና አደናጋሪ ምልከታዎች ሲገለጽ መሰንበቱ የሚታወስ ቢሆንም በሁለት ቀናት በዘለቀው ጠቅላላ ስብሰባ የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ደሕዴግ) ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ደሳለኝ ኃይለማሪያምን በዋና ሊቀመንበርነት ሲመርጥ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ደመቀ መኮነንን ደግሞ በምክትል ሊቀመንበርነት በመምረጥ ስብሰባውን ማጠናቀቁ ተገለጸ።

 

በድርጅቱ ደንብ መሰረት የኢህአዴግ ዋናና ምክትል ሊቀመንበር የሀገሪቱ ዋናና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ሲገለጽ የሰነበተ ሲሆን የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር አቶ በረከት በዚሁ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን አቶ ኃይለማሪያም የምክትልነቱን ቦታ ደግሞ አቶ ደመቀ እንደሚይዙ ለብሉምበርግ የዜና አውታር አሳውቀዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ