የግንቦት ሰባት ንቅናቄ በኑርንበርግ ህዝባዊ ስብሰባ ክፍል ፩
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. June 14, 2008)፦ ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዛሬ ረፋዱ ላይ በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ ከደጋፊዎቹና ከኢትዮጵያውያን የሚያደርገውን ህዝባዊ ውይይት መጀመሩ ታወቀ። በዚህ ህዝባዊ ውይይት የንቅናቄው መሥራቾች የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ መስፍን አማን እንደተገኙ ታውቋል።
በዚህ ህዝባዊ ውይይት ላይ የመጀመሪያው ተናጋሪ የነበሩት አቶ መስፍን አማን ሲሆኑ፣ በመቀጠል ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ንግግር አድርገዋል። ስብሰባው እረፍት አድርጎ ከተመለሰ በኋላ ከተሰብሳቢው ጋር ሰፊ ውይይት እያደረገ ይገኛል።
ውይይቱ በተለይም በፓልቶክ የኢትዮጵያን ከረንት አፌርስ ዲስከሽን የውይይት መድረክ ክፍል በቀጥታ እየተላለፈ ሲሆን፣ የአቶ መስፍን አማንን ንግግር ከዚህ በታች አቅርበነዋል። ቀሪውን ውይይት በድምፅ ለማቅረብ እንሞክራለን።
ንግግሩን ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን (Play Button) ይጫኑ!