አንድነት ፓርቲ ስድሳ የላዕላይ ም/ቤት አባላት መረጠ
ከፍተኛውን ድምፅ ያገኘችው ወ/ት ብርቱካን ነች
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. June 18 2008)፦ ዛሬ የተሰበሰበው የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ስድሳ የላዕላይ ም/ቤት አባላትን የመረጠ ሲሆን፣ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ በከፍተኛ ድምፅ በአንደኛ ደረጃ ስትመረጥ ኢንጂንየር ግዛቸው በሁለተኛ ደረጃ መመረጣቸው ታወቀ።
ለኢትዮጵያ ዛሬ በደረሰው መረጃ መሰረት ሦስት መቶ የሚሆኑ የጠቅላላ ጉባዔው ተሰብሳቢዎች 105 ተመራጮችን የጠቆሙ ሲሆን፣ ከዚሁ አኀዝ ላይ ስድሳዎቹን ለመምረጥ ስድስት ሰዓታት በፈጀው የቆጠራ ሂደት ላዕላይ ምክር ቤቱ አባላት ተመርጠዋል።
ለላዕላይ ምክር ቤት አባልነት ከተመረጡት ውስጥ ወ/ት ብርቱካንንና ኢንጂንየር ግዛቸውን ጨምሮ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፣ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም፣ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ፣ ወጣት ስለሽ ጠና እና ሌሎችም የተካተቱ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የላዕላይ ምክር ቤት አባላቱ 18ቱን ሥራ አስፈጻሚ አባላት ለመምረጥ መሰብሰባቸውን ለማወቅ ችለናል።
ሂደቱን እየተከታተልን ተጨማሪ ሪፖርት ለማቅረብ እንሞክራለን።
ኢትዮጵያ ዛሬ



