ቤተክርስቲያናቸውቋሚቤተመቅደስአግኝታለች

በጥቅምት 2009 .. የብሪቲሽ ኮሉምቢያ ጠቅላይ ፍርድቤት 1990ዎቹ መጀመሪያ በሊቀካህናት ምሳሌ እንግዳ ቤተክርስቲያን ስር፡በነአቡነ ዜናማርቆስ ቡራኬ የተመሰረተውን የቫንኩቨር ቅድስት ማርያም ቤተክርትስቲያን አንስቶ ወደ ኢህአዴግ ለሚያጋድለው ስብስብ እንዲሰጥ ሲወስን፡ በስደተኛው ሲኖዶስ ስር የሚገኙ የቫንኩቨር ማርያም ልጆች አዝነው ነበር። የፍርድ ቤቱ ክርክር ሂደት በወቅቱበ ኢትዮጵያ ዛሬና በሌሎች ድረገጾች ላይ ተዘግቧል።ልምዱ ለሌሎችም ይጠቅም ዘንድ ወደፊትም እናትትበታለን።

 

ከዚያ አሳዛኝ የፍርድቤት ውሳኔ በሁዋላ የተራረፉትም እመናን ተሰብስበው ህብረታቸውን አጠናክረው በመቀጠል፤ በሂደቱ አንዳንድ እንቅፋቶች ቢያጋጥሙም፤ እነሆ ከብዙ እንግልትና ትጋት በሁዋላ፤ ከስፍራስፍራ፤ ከአዳራሽ አዳራሽ ስትንከራተት የነበረችው ቤተክርስቲያን ማረፊያ ቤተ መቅደስ አግኝታ፤ በነገው እለት፤ ማለትም እሁድ ኦገስት 4 ቀን፤ 2013 .. አዲሱ ቤተመቅደስ በይፋ ትውውቅና ምረቃ ይደረግበታል።

 

ይሄንን 100 በላይ እድሜ ያለውንና በጥንታዊቷ የብሪቲሽ ዋና ከተማ፡ ኒውዌስትሚኒስተር፡ 628 ሮያል መንገድ ላይ የሚገኘውን ቤተመቅደስ በቫንኩቨር፡ ካልጋሪ፤ ሲያትል፤ ፖርትላንድና አካባቢው የሚገኙ ምእመናን ተገኝተው ምረቃ ያደርጉለታል።

 

በእለቱ 4ኛው የቫንኩቨር ኢትዮጵያ ፌስቲቫልና የምእራብና ሰሜን አሜሪካ ከተሞች የእግርኳስ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን፡ ለፌስቲቫሉና ለእግርኳስ ጨዋታ ውድድሩ ከጎረቤት አገሮች የሚመጡ ኢትዮጵያዊያን ለቤተመቅደሱ ምረቃ በዓል ድምቀት እንደሚሰጡት ይጠበቃል።

 

ይሁንእንጂ፤ በቤተመቅደሱ መገኘት የተደሰቱና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የቤተክርስቲያኒቷ የረጅምግዜ አባል፡ በስደት የሚገኘው ሲኖዶስም ይሁን የአገረስብከቱ ሊቀጳጳስ ተደጋጋሚ ደብዳቤ ቢጻፍላቸውምና በበአሉ ላይ ተገኝተው ቡራኬ እንዲሰጡ ቢጋበዙም፤ እስካሁን ድረስ ምላሽ አለመስጠታቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

 

ምእመኑ ቫንኩቨር በካናዳ የምትገኝ ከተማ ብትሆንም አንድ ቀን ከሚያስጉዘው ከካልጋሪ ይልቅ ሁለት ሰዓት ለምትርቀው ሲያትል ስለምትቀርብ የቤተክርስቲያናቸው ሰበካ ወደሲያትል ዋሽንግተን እንዲጠቃለል እንደ ሚፈልጉ ተናግረዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ