በአውስትራሉያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መካከል በየዓመቱ የሚደረገው የስፖርት ውድድር ዘንድሮም ለ17ኛ ግዜ ከዲሴምበር 24 እስከ 29 ባለት 6 ቀናት በድምቀት ተከናውኗል። በዘንድሮው ውድድር ከመቼውም ግዜ በበለጠ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኢትዮጵያዊ የተሳተፈበት ነበር።

 

በውድድሩ የተካፈሉት የቡድኖች ብዛትና በቡድኖቹ መካከል ዋንጫ ለማንሳት የነበረውም ፉክክር ከመቼው ግዜ በላይ ደመቅ ያለ ሆኖ አልፏል።

የዘንድሮው ውድድር ካለፉት አራትና አምስት አመታት ውድድሮች ለየት የሚያደርገው በግለሰቦች ይዘጋጅ በነበረ ተቀናቃኝ ውድድር ሳቢያ ይፈጠር የነበረው ውዝግብ ተወግዶ ኢትዮጵያዊ ሁሉ አንድ ሆኖ ወደ አንድ የስፖርት ውድድር መሄድ መቻሉ ሲሆን፤ ይህ አንድነት ተመልሶ ሊገኝ የቻለውም በሜልበርን የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ባደረገው ያላሰለሰ ትብብርና ህብረት ነበር።

ከዚህም በተጨማሪ ዓመታዊ ውድድሩን ያዘጋጀው በሜልበርን የኢትዮጵያን ኮሚኒቲ የስፖርት ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም ያልተሞከሩ ውድድሮችን ማካተቱ ለዓመታዊ ውድድሩ ከፍተኛ ድምቀት ሰጥቶታል። ለስድስት ቀናት በተካሄዯው በዚሁ ውድድር 11 ቡድኖች ተሳታፊ ከሆኑበት ከዋናው ውድድር በተጨማሪ በአባቶችና በህጻናት ቡድኖችም መካከል ውድድሮች ተደርገዋል።

በዋናው ውድድር ኢትዮ-ስታር እና ሴቱቱ ሁመራ ለዋንጫ ቀርበው ኢትዮ ስታር 4 ለ1 በመርታት ዋንጫውን አንስቷል። በሜልበርን በተደረገው ውድድር ከኒውዚላንድና ከሲድኒ የመጡ ቡድኖች ተሳታፊ ሆነዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ