እስራኤልን ለአምስት ዓመታት መርተዋል
አርኤል ሻሮን  Ariel SharonEthiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 3 ቀን 2006 ዓ.ም. Jan 11, 2014)፦ የእስራኤል የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩትና ሀገሪቷን ለአምስት ዓመታት ያህል የመሩት አርኤል ሻሮን በሰማንያ አምስት ዓመታቸው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

 

አርኤል ሻሮን የእስራኤል አስራ አንደኛ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሆኑ፣ ከእ.ኤ.አ. 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በስትሮክስ በሽታ ተይዘው ህይወታቸው እስካለፈ ድረስ በህክምና የቆዩ ሲሆን፣ ለሞታቸው መንስኤ የሆነውም የዚሁ በሽታ ጠንቅ እንደሆነ ታውቋል።

ሻሮን የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን ከመቆናጠጣቸው በፊት በልዩ ልዩ የመንግሥት ኃላፊነት ቦታ የሰሩ ሲሆን፣ በውጪ ጉዳይ ሚንስትርነትም አገልግለዋል።

እ.ኤ.አ. ፌብሪዋሪ 26 ቀን 1928 ዓ.ም የተወለዱት አርኤል ሻሮን ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ