Anna GomezEthiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. July 18, 2008)፦ የአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና ዲፕሎማት የሆኑት ሚስ አና ጐሜዝ የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች በቡድን 8 ሀገሮች ጉባዔ ላይ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ከሚወቀሱ የአፍሪካ መሪዎች ጋር መሆን ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ ያላቸው አመለካከት ዝቅተኛ ነው በማለት ወቀሱ።

 

አና ጐሚዝ ዩሮ አክቲቭ ከተባለ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ እንደገለፁት በቡድን 8 ስብሰባ ላይ ሁሉም መሪዎች በዚምባቡዌ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ፍላጐታቸውን በሚያሳዩበት ወቅት፣ በዚያው አንፃር በስብሰባው ላይ በሰብአዊ መብት ረገጣ የሚወነጀሉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በጉባዔው ላይ እንዲካፈሉ በማድረግ ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ ያላቸውን ምልከታ የተዛባ መሆኑን አሳይተዋል ብለዋል።

 

በቶኪዮ የግሩፕ 8 ስብሰባ ላይ ከአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች መካከል ኮሚሽነሩ ባሮስ በተገኙበት ፕሮግራም የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ከሀገር ሀገር ለያይተው ማየታቸው፣ ሁሉንም መሪዎች በሰብዓዊ መብት ጉዳይ ደካማ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል። 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ