በስድስት ሠራተኞችም ክስ ቀርቦባቸዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን 2000 ዓ.ም. July 19, 2008)፦ በአሸባሪነት ተጠርጥረው የተያዙ 28 እስረኞችን በዋስ ለቀዋል በሚል በቀረባበቸው የዲሲፕሊን ክስ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሥራ እግድ የተጣለባቸው ዳኛ ኑሩ ሰዒድ የተከሰሱበትን ጉዳይ አስመልክተው ለዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በደብዳቤ መልስ መስጠታቸውን ምንጮች ጠቆሙ። በዳኛው ላይ በስድስት የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችም ክስ ቀርቦባቸዋል።

 

በዳኛው ላይ ከቀረበው የፍትህ ሚኒስቴር ክስ በተጨማሪ ስድስት የፍርድ ቤቱ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ዳኛው እንደሚሰድቧቸውና እንደሚያመናጭቋቸው በመግለጽ ፍርድ ቤቱ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ሥራ ለመልቀቅ እንደሚገደዱ ገልጸው ማመልከታቸው ታውቋል።

 

ፍትህ ሚኒስቴር መጋቢት 9 ቀን 2000 ዓ.ም. ለፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት ካቀረበው የዲሲፕሊን ክስ በተጨማሪ በሠራተኞቹ የቀረበባቸውን ክስም በሚመለከት አብረው መልስ እንዲሰጡ በተሰጣቸው ደብዳቤ መሰረት መልስ መስጠታቸው ታውቋል።

 

ዳኛ ኑሩ ሰዒድ ከዳኛ ሀብታሙ ወርቁ እና ከዳኛ ሰዒድ ሐሰን ጋር በመሆን፣ በጅጅጋ ከተማ ባስቻሉት ተዘዋዋሪ ችሎት በአሸባሪነት የተጠረጠሩ 28 እስረኞችን በዋስ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል በሚል የዲሲፕሊን ክስ የደረሰው የፌደራል ዳኞች አስተዳደር፣ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ሰጥተዋል ከተባሉት ሦስት የፌደራል ፍ/ቤት ዳኞች መካከል ዳኛ ኑሩ ሰዒድ በተጨማሪም በስድስት ሠራተኞች በመከሰሳቸው ላልተወሰነ ጊዜ ከዳኝነት ሥራቸው እንዲታገዱ መወሰኑና፣ ክሱ ከደረሳቸው ቀን አንስቶ በ10 ቀን ውስጥ መልስ እንዲሰጡ በተገለጸላቸው መሰረት መልስ መስጠታቸው ታውቋል።

 

የዲሲፕሊን ክሱን በተመለከተ በደብዳቤ መልስ የሰጡት ዳኛ ኑር ሰዒድ፣ መልስ እየተጠባበቁ መሆኑንም ምንጮች ጠቁመዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ