በስዊድን የደብረ ታቦር በዓል ተከበረ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. August 20, 2014)፡- በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በሚገኘው የደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የደብረታቦር በዓል በደማቅ ሁኔታ በትናንትናው ዕለት ተከበረ። ጸሎትና ትምህርቱ በኃይማኖት አባቶች ለምዕመናኑ ከተሰጠ በኋላ፣ ከምሽቱ አንድ ሰዓት (19፡00 ሰዓት) ላይ የበዓሉ መገለጫ የሆነው ችቦ በርቷል።

ይህ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ለሐዋርያቱ የተገለጸበት ቀንን በማሰብ የሚከበር ሲሆን፣ ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብህረ ሄዋን አውጥቶ ብርሃን ለብሶ ስለታያቸው የችቦ ማብራቱ ሥርዓት ይሄንንኑ በማሰብ እንደሆነ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የኃይማኖት መጻሕፍት ጠቅሳ ታስተምራለች።





