ዮሃንስ ደሳለኝ (በርሊን -ጀርመኒ)

Ethiopia Zare ሐሙስ ኅዳር 24 ቀን 2007 ዓም December 4, 2014  ከደች ባንክ ብድር ለመጠየቅ ረቡዕ ለታ ከጀርመኗ ቻንስለር መርከል ጋር ውይይት ለማድረግ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝን በመቃወም በርካታ ኢትዮጵያዊያን በቦታው በመገኘት ተቃውሟቸውን ማስማታቸው ታወቀ፡፡



      ከ 9am-12 :00pm የተደረገው ሰልፍ ሩት ጋርት ከሚባለው
ስፍራ ተነስቶ በብራንደርግ ጌት አልፎ ዋናውን የደች ባንክ አካሎ ዋና ዋና የፓርላማ ቢሮዎች በር ላይ በመቆም መልዕክታቸውን ካስተላለፋ በሁዋላ ወደ ቻንስለርዋ አቅንቱዋል ፣ በወቅቱም ኢትዬጵያዊ ጨዋነት የተሞላበት እና ትክክለኛና ወቅታዊ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ኢዮጵያዊያኑ በተለይ አቶ ኃይለማርያም በሚያልፉበት ሰዓት ከፍተኛ ድምጽ በመጠቀም  አስፈላጊውን መልዕክት አድርሰዋል።

- ጀርመን እንደ ኃይለማርያም ያሉትን አምባ ገነን መርዳት አቁሚ

- ዶች ባንክ ዕርዳታችሁ ገበሬ ማፈናቀያ ነው (stop land garbing)

- ጋዜጦኞችና ጦማርያን ይፈቱ

  - freedom &justice  now

  - ወያኔ ይውደም እና ሌሎችም በአማርኛና በጀርመንኛ ቋንቋ የተዘጋጁ መፈክሮች ተስተጋብተዋል፡፡

ሰልፋን ያዘጋጁት የበርሊንና የፍራንክፈርት  ነዋሪዎች ሲሆኑ በተለይ የአገራቸውን ችግር ለዓለም አቀፉ ማህበረስብ ለማሳወቅ የፍራንክፈርት ናዋሪዎች ሌሊቱን ለ7ሰዓት ያህል ተጉዘው የደረሱ ሲሆን ሰልፈኞቹ ለጀርመን ቻንስለር፡ ለፓርላማ አባላትና ለአውሮፓ ህብረት ኢትዬጵያ ውስጥ ያለውን ጥልቀት ችግር የሚገልጽ ደብዳቤ በማዘጋጀትና በስፍራው የተገኙ ከ500 በላይ ስልፈኞችን ጨምሮ በርካታ ስወች የተሳተፉበት ፒቲሽን ፈርመው ለሚመለከተው አካል አስግብተዋል፡፡

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ