በጀርመን፣ ፍራንክፈርት የተደረገው ሰላማዊ ስልፍ ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ
ዮሐንስ ደሳለኝ - (ጀርመን)
Ethiopia Zare ቅዳሜ ጥር 10 ቀን 2007 ዓም January 17, 2015:- ባሳለፍንው ሰኞ በፍራንክፈርት የሚገኙ ኢትዩጽያዊያን በአሁኑ ሰዓት በአገራቸው የሚደረገውን የመብት ጥሰት ለተለያዬ ተቁማት ለማሳወቅ ሁለት ሰዓት የፈጀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። መነሻውን ከዋናው የባቡር ጣቢያ አንድ ጣቢያ (station)አልፉ በሚገኘው ታውንስላገን አካባቢ ከዋናው ደች ባንክ አጠገብ ያደረገው ሰልፍ፣ ረፈዱ 11፡00am ላይ ተጀምሮ የእንግሊዝ ኤምባሲን አካሎ ምሳ ሰዓት ላይ (1፡00pm) ፍራንክፈርት የሚገኘው ኢትዬጽያ ቆንጽላ ጽ|ቤት በመገኘት በተለመደው ኢትዬጵያዊ ጨዋነት ተጠናቁል።
EPCOU(Ethiiopian poltical and civic organization ) ያዘጋጀው ይህ ሰልፍ አላማው በአሁኑ ሰዓት በስልጣን ላይ ያለው አምባገነን የህወሀት መንግስት በኢትዬጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ደባ ለተለያዩ የመንግስት አካላትና የገንዘብ ተቁማት ለማሳወቅ ነው ፤በዕለቱ ቁጥራቸው እስከ 150 የሚገመት ከተለያዬ የጀርመን ከተሞች የመጡ ኢትዬጵያዊያን የተካፈሉ ሲሆን የጃንዋሪ ወር ብርድና ዝናብ ሳይበግራቸው እጅ ለእጅ በመያያዝ ለደች ባንክ ሠራተኞችና ኃላፊዎች መልዕክታቸውን በጹሁፍና ከዚያም በድምጽ አሰምተዋል፣በተለይ በአሁኑ ሰዓት መንግስት ለመሸጥ እየተዘጋጀ ያለውን ሶቨርጅን ቦንድ በመቃወም የሚከተለውን መፈክር አሰምተዋል።
ጀርመን አምባገነኖችን መርዳት ያቁም!
የወያኔ መንግስት አሸባሪ ነው!
stop land garbing ና የመሳሰሉትን መፈክሮች በማሰማት ቀጣይ ጉዞ ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ ሆኑዋል እዚያም በኤምባሲው ቆንስላ በር ላይ በመገኘት ፤
እንግሊዝ አንዳርጋቸው ዜጋሽ የት ነው ያለው ፣አንዳርጋቸው አሸባሪ አይደለም የነጻነት ታጋይ እንጅ ፤ ነጸነት ነጸነትነጸነት ። የሚሉ መፈክሮችን አስተጋብተዋል ፣ይህ እንዳለቀም በዚያው ስሜት ረዘም ያለ ጉዞ ተደርጎ ኢትዬጵያ ኤምባሲ ቆንጽላ ጵ|ቤት በመሄድ በከፍተኛ ጬህት በታገዘ ድምጽ መልዕክት አስተላልፈዋል
ጋዜጠኞችና ጦማሪን ይፋቱ!
አሸባሪ ራሱ ወያኔ ነው!
ኃይለማርያም አይወክለንም!
ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!
ወያኔ የታሪክ አተላ ። የሚል ነበር። ከኤምባሲው ምንም ዓይነት መል ባይሰጥም፣ እንዲያውም አንድን አገር እወክላለሁ ከሚል ኤምባሲ በማይጠበቅ ሁኔታ ክፍት የነበረውን መስኮት ዘግተው ተቀምጠው ተስተውለዋል።



