አቶ አብዲ መሐመድ ኦማር አስነዋሪ መልስ ሰጡ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አብዲ መሐመድ በዋሽንግተን ዲሲ ለደረሰባቸው ተቃውሞ የሰጡት መልስ ከባለሥልጣን አንደበት የማይወጣ አስነዋሪ እንደነበረ ተገለጸ። ሥርዓቱ እንዲህ አይነት ሰዎችን ያቀፈ ነው ያሉት ታዛቢዎች ከተቃዋሚዎች ጋር የተደረገውን አንባጓሮ በቪድዮ በመቅረጽ ለህዝብ አቅርበዋል።
በቪዲዮው ላይ እንደሚደመጠው የአስተዳዳሪውን አባባል እዚህ ላይ ለመጥቀስ የተቆጠብን ሲሆን፣ አስተዳዳሪው ይህን ቃል ለማውጣት የቻሉት ስራቸውንና ሰውየውን ለይተው ያወቁት ተቃዋሚዎች ባገኙቸው ጊዜ «ይህ ሰው በሱማሌ ክልል ወንጀል የፈጸመ ነው። ነፍሰ ገዳይ ነው፣ የዘር ማጥፋ ያካሄደ ነው። አንተ የሱማሌዎች ደም ያለብህ ስትሆን እዚህ ምን ልትሰራ መጣህ?›› በማለት በተናገሯቸው ጊዜ እንደሆነ ለማውቅ ተችሏል።
ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት የአሜሪካ የጸጥታ አባላት በቦታው ተገኝተው ግርግርሩን ያረጋጉ ሲሆን፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት የሞባይል ካሜራቸውን ከፍተው ቪዲዮ በመቅረጽ ወደኋላቸው እየሸሹ ያችኑ የብልግና ስድባቸውን እየደጋገሙ ሲናገሩ ተስተውለዋል።



