ነፍሰ ገዳዩ ጆን ኢትዮጵያ ውስጥ ጓደኛ አለው ተባለ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የአይሲስ ዋንኛ አራማጅ ነው የተባለው ጆን (መሐመድ ኤምዋዚ) የቅርብ ጓደኛው እንግሊዛዊው ዓሊ አድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር እንደሚገኝ በተለያዩ የብዙኀን ዜና ማሰራጫዎች እየተናፈሰ ይገኛል። መሐመድ ኤምወዚ በማለት ራሱን ሰይሞ የቆየው ይህ ግለሰብ፣ የኩዌት ዝርያ የሆነ እንግሊዛዊ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፤ አንገት ቀልቶ ገዳዩ በሎንደን ከተማ ኮሌጅ ውስጥ ይማር እንደነበር ታውቋል።
ጆን ከዓሊ ጋር የቅርብ ጓደኝነት እንዳለውና በኢትዮጵያ እስር ቤት እንደሚገኝ መታወቁን አስመልክቶ ሁኔታውን እንዲያብራሩ የተጠየቁት የኢትዮጵያ ባለስልጣን "ጽንፈኞቹ የሀገራቸው ተጨባጭ ስጋት እንደሆኑ ገልጸው፤ ሆኖም ይሄንን ካወቅን የቆየን በመሆናችን ተገቢውን የመከላከል እርምጃ ስናደርግ ቆይተናል" ብለዋል። አያይዘውም የምዕራቡ ዓለም የዜና አውታሮች የጆን ጓደኛ ኢትዮጵያዊ ነው ብለው ያቀረቡት ዜናም እኛን ብዙም አያደናግጠንም፣ የሁኔታውን ግብአት ግን እንጠቀምበታለን በማለት ተናግረዋል።
ዓሊ አድሮስ በሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት፣ የአራት ዓመት ከስድስት ወር ተፈርዶበት በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛል።



