62 ሕፃናት ተገድለዋል
People gather at the site of an air strike at a residential area near Sanaa (Reuters)

Ethiopia Zare (ሐሙስ መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ.ም.፣ April 2, 20015)፡- የየመን ሑቲ ሚሊሽያ አማጽያንን ለማጥቃት በሳውዲ ዐረቢያ መሪነት በየመን ላይ እየተወሰደ ያለው የአየር ድብደባ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ታወቀ። ለሣምንት በዘለቀው የአየር ጥቃት 62 ሕፃናት መገደላቸውን ዩኒሲኤፍ ገለፀ።

ባለፈው ሰኞ በዩኤንኤችሲአር ስር ያለውን ማዝራቅ የተሰኘውን በሐጃ ክልል የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ላይ የአየር ድብደባው በመፈፀሙ 45 ሲቪሎች ሲገደሉ፣ ወደ 200 ሰዎች እንደቆሰሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። ዩኒሲኤፍ በበኩሉ በአንድ ሣምንቱ የአየር ጥቃት ቢያንስ 62 ሕፃናት መገደላቸውን አስታውቋል።

የዚህ አየር ጥቃት አራማጆች በመግለጫቸው የሑቲ ሚሊሽያ አማጽያን አገር ለቀው ካልወጡና በኃይል ሊገረስሱት የሞከሩትን፣ በአሁኑ ወቅት ስደት የሚገኘው እና በፕሬዝዳንት አብድራቡሕ መንሱር ሐዲ የሚመራው መንግሥት ወደቀድሞ ሥልጣኑ ካልተመለሰ ጥቃታቸውን እንደማያቆሙ አስታውቀዋል።

Unicef says at least 62 children have been killed in the past week of fighting

የአየር ጥቃቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ጨምሮ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ፍርሃት ሰፍኖ የቆየ ሲሆን፣ ሰሞኑን በተወሰደው ርምጃ የአማጽያኑ የመሣሪያ ማከማቻ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል። የስደተኛ መጠለያው መደብደቡን ተከትሎ እና በአገሪቱ ያለው ሰላም ላለማቋረጥ በመደፍረሱ፣ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ስጋትና ውጥረት ላይ መሆናቸውን ከስደተኞቹ ለመረዳት ችለናል።

በየመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያውያንን ከየመን ለማውጣት እያደረገ መሆኑ ታውቋል። በየመን በፖለቲካ ስደተኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ግን የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የማይችሉ በመሆኑ፣ በየመን ያለው ጦርነት በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ሕይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚወድቅና ድምፃቸው በዓለም ዙሪያ እንዲሰማላቸው ጥያቄ እያቀረቡ መገኘታቸውን ለማወቅ ችለናል።

በሳውዲ ዐረቢያ የሚመራው ይኸው ጣምራ የአየር ጥቃቱ አስር አገራትን ያቀፈ ሲሆን፣ ድብደባውን ለማካሄድ የተመደቡት የጦር ተዋጊ ጄቶች 100 ከሳውዲ፣ 30 ከተባበሩ ዐረብ ኢምሬቶች፣ 15 ከኩዌት፣ 15 ከባህሬን፣ 10 ከኳታር፣ ጥቂት ጄቶች ደግሞ ከዮርዳኖስ፣ ከሞሮኮ፣ ከሱዳን፣ እንዲሁም የባህር ኃይል ድጋፍ ደግሞ ከፓኪስታንና ከግብፅ መለገሱን አንድ የሳውዲ አማካሪ ገልጸዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ