አንድ የኢህአዲግ የፓርላማ አባል እንግሊዝ አገር ጥገኝነት ጠየቀ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነኀሴ 3 ቀን 2000 ዓ.ም. August 09, 2008)፦ አቶ በለጠ ኢታና የተባሉ የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ የፓርላማ አባል እና በፓርላማው የመንግሥት አስተዳዳር ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት በእንግሊዝ አገር ጥገኝነት መጠየቁ ታወቀ።
አቶ በለጠ በሐምሌ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. ወር ለንደን ወደሚገኘው ናሽናል ኦዲት ኦፊስ ተቁዋ ለአስር ቀናት ሥልጠና ከሄደ በኋላ በዚያው መቅረቱ ታውቋል። ጥገኝነቱን ለእንግሊዝ መንግሥት ያቀረበው እንግሊዝ ሀገር እንደገባ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል።
አቶ በለጠ ኢታና በ1997 ዓ.ም. በተደረገው ምርጫ ኢህአዴግን ወክሎ በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን በምርጫ ጣቢያ ”ሊሙ ኮሶ አንድ” ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወዳድሮ ለፓርላማ መመረጡን ለመረዳት ችለናል።
ከምርጫ 97 በኋላ ኢህአዴግን ጥለው ከሄዱት ባለሥልጣናት ውስጥ ሰሜን ዕዝ ውስጥ ግንባር ላይ የነበረው ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቺ የሚጠቀስ ሲሆን፣ የኢህአዴግን መንግሥትና መከላከያን በመተው ወደ ኤርትራ ገብቶ ኦነግን እንደተቀላቀለ መደመጡ አይዘነጋም።



