World bank

ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 8, 2016)፦ በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ ያለውን የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ገቢን ለማስተካከልና የወጪ ንግድ ምርቶች አቅርቦት እንዲጨምር ለማበረታታት፣ ኢትዮጵያ የብር የምንዛሪ ምጣኔን እውነተኛውን የኢኮኖሚ አቅሟን በሚያመላክት ደረጃ ማስተካከል ይገባታል ሲል አሳሰበ። አሁን ያለው የብር ምንዛሪ ሚዛኑን የሳተና ከእውነተኛ አቅሙ በላይ የገዘፈ መሆኑንም ጠቁሟል።

በአሁን ወቅት አንድ የአሜሪካን ዶላር በጥቁር ገበያ እስከ 27 ብር የሚመነዘር ሲሆን፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያም በርካታ የገቢ ንግድ ዘርፎች መቀዛቀዝ አሳይተዋል።

ባንኩ ማክሰኞ ኅዳር ፳፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. በሼራተን አዲስ ባካሄድው አምስተኛው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፖርት ካተኮረባቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው፣ ሚዛኑን የሳተው የብር የምንዛሪ ምጣኔ ጉዳይ እንደነበር ታውቋል። ከሪፖርቱ አዘጋጆች አንዱ የሆኑት ማይክል ጋይገር እንደገለጹት ከሆነ፣ የኢትዮጵያ የምንዛሪ ምጣኔ በተለይ እ.ኤ.አ. በ2010 ከተደረገው የምንዛሪ ማስተካከያ (Devaluation) በኋላ በዝግታ እየቀነሰ መሆኑ የታየ ቢሆንም፤ አገሪቱ በምትከተለው ቅይጥ ምንዛሪ ፖሊሲ ምክንያት (Managed Floating) አሁንም እውነተኛው የብር የምንዛሪ ምጣኔና በሥራ ላይ ያለው ምጣኔ በእጅጉ የተዛነፈ ነው።

በዚህ መሠረት እውነተኛውን የምንዛሪ ምጣኔ የሚለካው ʻሪል ኢፌክቲቭ ኤክስቼንጅ ሬትʼ (Real Effective Exchange Rate) የምጣኔውን መዛነፍ በግልጽ እንደሚያሳይ የገለጹት ሚስተር ማይክል፣ የምንዛሪ ማሻሻያው ከተደረገ በኋላ (2010) እንኳን የብር የምንዛሪ ምጣኔ ቢያንስ በ84 በመቶ ጨምሮ እንደሚታይ አስረድተዋል። በመሆኑም ብር የምንዛሪ ምጣኔውን ስቶ ከሚገባው በላይ መቆለሉን (Overvalue) ጠቅሰዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአገር ቤት ያሉ የንግድ ተቋማት የገቢው እየቀነሰ የመጣ ሲሆን፣ በርካታ ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸው የሚከፍሉት ደምወዝ እያጠራቸው ገመገኘታቸውም በላይ፤ ሠራተኞቻቸውን ከሥራ እያሰናበቱ እንደሚገኙ ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሱት መረጃዎች ይጠቁማሉ።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ