የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የተሻሻለው የመከላከያ ሠራዊት ደንብ ቁጥር 385/2008ን ነው

ኢዛ (ሰኞ ኅዳር ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 11, 2019)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ድንብና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ ማሳለፉ ተገለፀ።

ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን 2012 ዓ.ም. በተካሔደው 75ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ በቅድሚያ የተወያየበት አጀንዳ፤ ማሻሻያዎች ተደርገውበት ሥራ ላይ እንዲውል የተደረገው የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ ላይ መኾኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ ያደረገው መረጃ ያስረዳል።

በአዲሱ አዋጅ ከተካተቱ አዳዲስ አደረጃጀትና መዋቅሮች ጋር ለማጣጣም፣ በሥራ ላይ ባለው ደንብ የታዩ የአፈጻጸም ችግሮችን ለማስተካከል፣ የመከላከያ ሠራዊቱን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማቃለል የሚረዱ አዳዲስ ድንጋጌዎችን ለማካተት በሚያስችልና የመከላከያ ሠራዊቱን የግዳጅ አፈጻጸምና ሞራላዊ ዝግጁነት ለማጠናከር ሲባል የመከላከያ ሠራዊት ደንብ ቁጥር 385/2008ን ማሻሻል አስፈላጊ በመኾኑ የመከላከያ ሚኒስቴር ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ ማቅረቡ ታውቋል። ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየና ማሻሻያዎችን በማከል ደንቡ በሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑ ታውቋል።

በዚህ ደንብና ሌሎች ውሣኔ የተሠጠባቸው ጉዳዮችን በተመለከተ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ይፋ ያደረገው መረጃ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!