Ethiopian Information Network Security Agency (INSA)

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ

በአገሪቱ ለሃያ ደቂቃ ኢንተርኔት ተቋርጦ ነበር

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. December 5, 2019)፦ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረ የሳይበር ጥቃትን ለማክሸፍ ሲባል የአገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ለሃያ ደቂቃዎች ተቋርጦ እንደነበር ተመለከተ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ማምሻውን እንዳስታወቀው፤ ዛሬ ኅዳር 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረ ጥቃትን ለማክሸፍ ችሏል።

ጥቃቱን ሙሉ ለሙሉ ማክሸፍ መቻሉንና ይህንን የሳይበር ጥቃት ለመከላከልም የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲው በይነ-መረብ አገልግሎትን (ኢንተርኔትን) ከ15-20 ደቂቃዎች ለማቋረጥ አስገድዶት እንደነበር ተጠቅሷል።

የኤጀንሲውን ምክትል ዋና ዳይሪክተር ኢንጂንየር ወርቁ ጋቸናን በመጥቀስ ከኤጀንሲው የወጣ መረጃ እንደሚያስረዳው፤ ኤጄንሲው በአዋጅ ከተሠጠው ተግባራትና ኃላፊነቶች መሐል አንዱ የአገሪቱን የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መሠረተ ልማቶች ላይ ማናቸውንም የሳይበር ጥቃቶች መከላከል ነው። በመኾኑም ዛሬ ሊደርስ የነበረው ጥቃት ጉዳት ከማድረሱ በፊት በኢትዮ ሰርት መከላከል መቻሉን ኢንጂንየር ወርቁ ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ጥቃት ሊደርስ የነበረውን በየትኞቹ የፋይናንስ ተቋማት ላይ እንደነበር አልገለጸም።

ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ ኢትዮ-ቴሌኮምም ደቂቃዎች ተቋርጦ እንደነበር፤ የተቋረጠውም ኤጀንሲው ኔትዎርኩን በማቋረጡ ስለመኾኑ አረጋግጧል። ለዚህም ይቅርታ ስለመጠየቃቸውም በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የአንድ ማኅበራዊ ሚዲያ ገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ