Dr. Shumete Gizaw

ዶ/ር ሹመቴ ግዛው የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኾኑ

ዶ/ር ሹመቴ ግዛው የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኾነው ተሹመዋል

ኢዛ (ሐሙስ ጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 6, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከጸጥታና ከደኅንነት ጋር ለተገኛኙ ተቋማት ለአምስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ሹመት ሠጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሠጡት ሹመት መሠረት አቶ መስፍን መላኩን በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አድርገው ሾመዋል።

ከዚህ ሹመት ባሻገር ለኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋናና ምክትል ዳይሬክተር በመኾን የሚያገለግሉ አዲስ ተሿሚዎችን ሰይመዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በወጣው መረጃ መሠረት፤ ዶ/ር ዐቢይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኾነው እንዲያገለግሉ የሾሙዋቸው ዶ/ር ሹመቴ ግዛውን ሲሆን፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው የተሾሙት ደግሞ አቶ ከፍያለው ተፈራን ነው።

ሌሎቹ ሁለቱ ሹመት የተሠጣቸው ደግሞ፤ አቶ ወርቁ ጋቸናና አቶ ዘላለም መንግሥቴ ናቸው። በመረጃው መሠረት አቶ ወርቁ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምርና ልማት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ ዘላለም ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኾነው ተሹመዋል።

የዛሬው ሹመት በመረጃና ደኅንነት ዙሪያ በሚሠሩ ተቋማት ውስጥ የተሠጠ ከፍተኛ ሹመት ስለመኾኑ ያመላከተ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ