Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 17 ቀን 2000 ዓ.ም. January 26,2008)፦ ምርጫ 97ን አስከትሎ በተከሰተው የፖለቲካ ነውጥ በኢህአዴግ አመራር በግፍ የታሰሩ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ አባላትና ደጋፊዎችን የማስፈታት ሂደት በምክትል ሊቀመንበሯ የሚመራው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባቋቋመው የእስረኞችን ጉዳይ በሚከታተል ንዑስ ኮሚቴ አማካኝነት ከሽማግሌዎች ጋር በተደረገው ጥረት ቢያንስ 29 እስረኞች በቅርቡ ከእስር እንደሚለቀቁ ምንጮቻችን ገለጹ።

 

የቅንጅት መሪዎች ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሥራ አስፈጻሚው የተዋቀረውና በምርጫው ሰበብ የታሰሩ የቅንጅት አባላትንና ደጋፊዎችን በየአካባቢው በመከታተል ከሽማግሌዎቹ ጋር የሚሠራው ኮሚቴ ባደረገው ጥረት 23ቱ እስረኞች በቅርቡ እንደሚፈቱና ሌሎች በክፍለሀገር የሚገኙ ስድስት እስረኞችም በአጭር ጊዜ የፍቺ ሂደታቸው እንደሚጠናቀቅ እነዚሁ ምንጮቻችን ገልፀዋል። ይሄው በሥራ አስፈፃሚው የተዋቀረው ኮሚቴ ብዛት ያላቸው የእስረኞች ስም ዝርዝር በማሰማሰባ ላይ እንደሚገኝ ታማኝ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

 

የቅንጅት አመራሮች ከእስር ሲፈቱ ከአገር ሽማግሌዎቹ ጋር ከነበረው ስምምነት አንዱ በምርጫ 97 በተፈጠረው ግርግር የታሰሩ አባላትና ደጋፊዎቻቸው የነሱን መፈታት ተከትሎ እንደሚፈቱ ቢሆንም፤ ላለፉት አራት ወራት ጉዳዩ ሳይነሳ ቆይቷል። 

 

ይህን የተገነዘቡት የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች የበኩላቸውን እስረኞቹን ለማስፈታት የተቻላቸውን ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ፓርቲው ያቋቋመው አንድ ቡድን ፕሮፌሠር ኤፍሬም ይስኃቅ ከሚመሩት የሽምግልና ቡድን ጋር ተወያይተው ቢያንስ 29 እስረኞችን ለማስፈታት ጥረት ጀምሮ እንደነበር ተደምጧል። 

 

ፓርቲው ከሸምጋዩ ቡድን ጋር እንዲወያዩ የወከላቸው ከፍተኛ አመራሮቹ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ አቶ ግዛቸው ሽፈራው እና ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም መሆናቸው ታውቋል። 

 

እስረኞቹ ሊፈቱ የሚችሉት ይቅርታ ሲጠይቁ ብቻ በመሆኑ ፕ/ሮ ኤፍሬም ይስኃቅ እስረኞ ዘንድ በመሄድ የይቅርታ ደብዳቤው ላይ እንዲፈርሙ አድርገዋል። በዚህ ደብዳቤ መሰረትም እስረኞቹ በ15 ቀናት ውስጥ ከእስር ሊፈቱ እንደሚችሉ ታውቋል። 

 

እስረኞቹ እያንዳንዳቸው ከሦስት ወር እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት የተፈረደባቸው ሲሆን፣ ፍርድ ያላገኙ እና በይቅርታ መጠየቂያው ላይ ያልተካተቱ 33 ሌሎች እስረኞች ዝርዝር ለሽማግሌ ቡድኑ ተሰጥቶታል። 

 

ፍርድ አግኝተው ይቅርታ የጠየቁት ግለሰቦች ዝርዝር የሚከተለው ሲሆን፣ እነዚህ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙና በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ የተወሰነባቸው ናቸው።

1)   አቶ ዮሴፍ ገ/እግዚያብሔር፣

2)   አቶ ጌታዬ ወዳጄነህ፣

3)   አቶ ኤርሚያስ ሽፈራው፣

4)   አቶ ዮናስ መኰንን፣

5)   አቶ እንዳልካቸው ተስፋው፣

6)   አቶ ጋሻው ግርማ፣

7)   ብርሃኔ ካሳዬ፣

8)   አቶ ኤልያስ አዱኛ፣

9)   አቶ ሳሙኤል አበበ፣

10)   አቶ አያሌው ጥላሁን፣

11)   አቶ ዘነበ ዙላ፣

12)   አቶ ኡስማን ሱሌይማን፣

13)   አቶ ሽመልስ አሰፋ፣

14)   አቶ ብሩክ ታደሰ፣

15)   አቶ አሸናፊ ዮሐንስ፣

16)   አቶ ፍቃዱ ግርማ፣

17)   አቶ አዲሱ ባዴቻ፣

18)   አቶ አጥላባቸው አያሌው፣

19)   አቶ ክንዴ አያሌው፣

20)   አቶ ፋሲል አማረ፣

21)   አቶ ቱራ ጂማ፣

22)   አቶ ግዛቸው ግርማ እና

23)   አቶ ፍሬዘር ገ/ኪዳን የተባሉ 23 ግለሰቦች ናቸው።

 

ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ፡

1)   አቶ ተስፋሁን መስፍን፣

2)   አቶ ጌታቸው ሄኖክ፣

3)   አቶ ትዕዛዙ ከድር፣

4)   አቶ ፍሬዘር ጉያ፣

5)   አቶ አሸናፊ ማሞ እና

6)   አቶ ጉደታ ሚደቅሣ የተባሉ ግለሰቦችም በይቅርታ ጥያቄው ተካተዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!