Ethiopian Citizens for Social Justice

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ - ኢዜማ

እንደአዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ምስክር ወረቀት ለማግኘት እየተጠባበቀ ነው

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፳፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 1, 2020)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲያሟሉ ከጠየቃቸው ዝርዝር ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የኾነውን አንድ አገር አቀፍ ፓርት 10 ሺህ የአባላት ፊርማ ለምርጫ ቦርድ ማስገባት ሲሆን፤ ኢዜማ ከ18 ሺህ በላይ የአባላት ፊርማ ያለበትን ሰነድ ማቅረቡን አስታውቋል።

ይህንን መስፈርት ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎች ምርጫ ቦርድ የጠየቃቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ለምርጫ ቦርድ በማቅረቡ፤ እንደአዲስ የአገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ምስክር ወረቀት ለማግኘት እየተጠባበቀ መኾኑንም የፓርቲው የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ለፓርቲው ልሣን “የዜጎች መድረክ” ገልጸዋል።

በመጀመሪያ 5 ሺህ 615 የመሥራች አባላት ፊርማ ዝርዝር ከሁሉም ክልሎች ተሰብስቦ ገብቶ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው፤ ቀሪውን እንዲያስገቡ በተጠየቀው መሠረት ተጨማሪ 12 ሺህ 659 ፊርማ ማስገባታቸውንና ይህም ለምርጫ ቦርድ የገባው የፊርማ ዝርዝር 18 ሺህ 274 መኾኑን ገልጸዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ