የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የጻፈው ደብዳቤ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የጻፈው ደብዳቤ

ነገ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ ከማስረጃ ጋር እንዲቀርብ ነው የተጠየቀው

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 4, 2020)፦ ኢዜማ (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ) በአማራ ክልል፤ በጎንደርና በደብረሃን ከተሞች ያዘጋጃቸውን ሕዝባዊ ስብሰባዎች በአግባቡ ለማካሔድ እንዳይችል የተደራጁ ኃይሎች ችግር የፈጠሩበትና ይህንንም የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ከማስቆም ይልቅ፤ ተባብረው ስብሰባዎቹን አደናቅፈውብኛል በማለት ማመልከቱን ተከትሎ፤ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ማብራሪያ እንዲሠጥ አሳሰበ።

በዚህም መሠረት ስለጉዳዩ ሊያስረዱ ከሚችሉ ኃላፊዎች ጋር ነገ የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ በቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ በደብዳቤ ተጥይቋል። በዚሁ ደብዳቤ ላይ ኢዜማ ያቀረበውን ቅሬታዎች ማስረዳት የሚችል ኃላፊ ከማስረጃ ሰነዶች ላይ ነገ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት እንዲገኙ ጠይቋል።

ኢዜማ ጥር 17 ቀን በጎንደር ከተማ እንዲሁም ጥር 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በደብረብርሃን ከተማ ሊያካሒድ አቅዶአቸው የነበሩትን ሕዝባዊ ስብሰባዎች ማድረግ ሳይችል መቅረቱን፤ ለምርጫ ቦርድ የካቲት 10 ቀን በደብዳቤ ቁጥር “ኢዜማ/0480/12” ነበር ያሳወቀው። (ኢዛ)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የጻፈው ደብዳቤ (ገጽ 1)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የጻፈው ደብዳቤ (ገጽ 1)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የጻፈው ደብዳቤ (ገጽ 2)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የጻፈው ደብዳቤ (ገጽ 2)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ