ዓለም ባንክ 500 ሚሊዮን ዶላር የስምምነት ሰነድ አጸደቀ
የዓለም ባንክ
ግማሹ እርዳታ፤ ግማሹ ብድር መኾኑ ታውቋል
ኢዛ (ቅዳሜ መጋቢት ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 21, 2020)፦ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ500 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍና ብድር መፍቀዱንና ለዚህም የሚኾን ስምምነት ሰነድ ማጽደቁ ታወቀ።
በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ መሠረት ለኢትዮጵያ ከተፈቀደው 500 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 250 ሚሊዮን ዶላሩ በቀጥታ የሚሠጥ እርዳታ ነው።
ቀሪው 250 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔ በብድር የሚሠጥ እንደኾነ ተጠቅሷል።
ይህ የዓለም ባንክ ብድርና እርዳታ በዋናነት አገሪቱ ለጀመረችው አገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ ለሚተገበሩ ፕሮግራሞች የሚውል ነው። (ኢዛ)



