በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል

Ethiopia Zare (እሁድ ጥር 18 ቀን 2000 ዓ.ም. January 27,2008)፦ በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰኞ ጥር 19 ቀና 2000 ዓ.ም. የጠቅላላ ላዕላይ ምክር ቤት ስብሰባ መጥራቱን ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ።

እነኝሁ ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴው አንዳንድ ሊወሰኑባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ለመነጋገር በሚል ለጠቅላላ ላዕላይ ኮሚቴ አባላት ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ነገ ሰኞ ላዕላይ ምክር ቤቱን ሥራ አስፈጻሚው ጠቅላላ ጠርተዋል።

በቅንጅቱ ውስጥ በተከሰተው አለመግባባት ምክንያት ካሉት ጠቅላላ የምክር ቤቱ አባላት 27ቱ በወይዘሪት ብርቱካን የሚመራውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንቅስቃሴ የሚደግፉ ሲሆን፣ 6ቱ በኢ. ኃይሉ ሻወል የተወከሉትን አቶ አባይነህ ብርሃኑ ጋር የሚተባበሩ ናቸው። ቀሪዎቹ ራሳቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ከፓርቲው ያገለሉና ወደ ውጭ ሀገር የተሰደዱ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!