የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ስብሰባው የተካሔደው በቪዲዮ ኮንፈረንስ ነው

ኢዛ (ቅዳሜ መጋቢት ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 4, 2020)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 26 ቀን ባካሔደው 81ኛ መደበኛ ስብሰባው በኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን ረቂቅ አዋጅና የኤካ ኮተቤ ሆስፒታልን ለማቁቋም በቀረበው ረቂቅ ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በቪዲዮ ኮንፈረንስ የተካሔደው የዛሬው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስበሰባ፤ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ረቂቆች ውስጥ አንዱ የኾነው የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን ረቂቅ አዋጅ፤ የኤሌክትሮኒክ ንግድና የኤሌክትሮኒክ የገንዘብ ዝውውርን ሕጋዊ እንዲኾኑ የሚያስችል እንደኾነ ተጠቅሷል። ይህ ረቂቅ እንዲጸድቅም ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቷል።

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታልን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ግን በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ