Ethiopian Public Health Institute

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 9, 2020)፦ በኮሮና ቫይረስ የሞተ ሰው አስክሬኑ ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓጓዝ ወይም እንዳይገባ ይደረግ ዘንድ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ይህንን ያስታወቀው፤ በኮሮና ቫይረስ የሞተ ሰው አስከሬን በሚነካካበት ወቅት በሽታው ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ የሚችል በመኾኑ ነው።

ከዚህ ሥጋት እንፃር ኢንስቲትዩቱ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን በጻፈው ደብዳቤ፤ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ አየር መንገዶች በኮሮና ቫይረስ የሞተ ሰው አስክሬን ይዘው እንዳይመጡ ለሁሉም አየር መንገዶች እንዲያሳውቅለት ጠይቋል።

ይህም ከየትኛውም አገር ወደ ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሞተ ሰው አስክሬን የማይገባ መኾኑን ያመላከተ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ