የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
የወንጌላውያን ካውንስል ሕጋዊነትን የሚያረጋግጥ አዋጅ ይጽደቅ ብሏል
የልማት ባንክን የማቋቋሚያ ስዋጅ እንዲሻሻል ወስኗል
ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 7, 2020)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ባካሔደው ሃያኛው አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ማቋቋሚያ ደንብ እንዲሻሻል ውሳኔ ሲያሳልፍ፤ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ሕጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ እንዲጸድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ስብሰባው ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ፤ የብሔራዊ ትርናፖርት ፖሊሲ እና የሎጅስቲክ ፖሊሲዎች ይገኙበታል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በተመለከት የተሰጠው መግለጫ የሚከተለው ነው። (ኢዛ)




