የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የመቀሌውን ግድያ አወገዘ

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ
ድርጊቱ በትግራይ የሰላምና ዴሞክራሲ እጦት ማሳያ ነው ብሏል
ኢዛ (ማክሰኞ ግንቦት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 19, 2020)፦ ከሁለት ቀናት በፊት በመቀሌ ከተማ ለአንድ ወጣት ሕይወት ሕልፈትና ለሁለት ወጣቶች የምቁሰል አደጋ በትግራይ ክልል ውስጥ የሰላምና ዴሞክራሲ እጦት ማሳያ ነው ሲል፤ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ዛሬ (ማክሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም.) ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማስተዳደርና የማስፈጸም አግባቦች ውስጥ የሰውን ልጅ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን ማክበርና በሕግ የማስከበር ተግባር ላይም የጸጥታ አካላት የላቀ ሰብአዊነት፣ ታጋሽነትና ፍጹም ሕዝባዊነትን የተላበሱ መኾን ይገባቸዋልም በማለት በመግለጫው ጠቅሷል።
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተፈጸመውን ግድያ በአወገዘበት በዚህ መግለጫ፤ በተለይ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ወጣቶች ላይ መተኪያ የሌለውን ክቡር ሕይወታቸውን እስከመቅጠፍ የደረስ የኃይል እርምጃ በየትኛውም መለኪያ መወገዝ ያለበትና ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እኩይ ተግባር ነው በማለት፤ ዛሬ አመሻሽ ላይ ገልጿል። የጽሕፈት ቤቱን ሙሉ መግለጫ አስነብበኝ! (ኢዛ)