ታደሰ ካሣ

አቶ ታደሰ ካሣ

20 ሺሕ ብር እንዲቀጡ ተወሰነ

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 21, 2020)፦ በቅርቡ ከነአቶ በረከት ስምኦን ጋር ስምራት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳ፤ በሌላ የክስ መዝገብ ተጨማሪ የስምንት ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራትና 20 ሺሕ ብር እንደተቀጡ ተገለጸ። ጉዳዩን የያዘው የባሕር ዳር ዙሪያ ፍርድ ቤት በአቶ ታደሰ ላይ ይህንን ቅጣት ያሳለፈው።

ጥረት ኮርፖሬትን በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ይመሩ በነበረበት ወቅት ከሌሎች ጋር በመተባበር ሥራን በማያመች መንገድ መርተዋል በሚልና ከዚሁ ጋር በተያያዙ የተለያዩ የሙስና ክሶሽ ጥፋተኛ ኾነው በመገኘታቸው ነው ተብሏል።

አቶ ታደሰ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ቅጣቱ ሊወሰንባቸው እንደቻለ የሚገልጸው መረጃ፤ የተከሳሹን ዕድሜ፣ የጤና ሁኔታ፣ ሕዝብንና አገርን ያገለገሉና፣ የቤተሰብ ኃላፊ መኾናቸው በቅጣት ማቅለያነት በችሎቱ ተይዞላቸው እንደነበር ተጠቅሷል።

በአቶ ታደሰ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ የነበሩ ሁለት ተከሳሾች ከሁለት ዓመት ከ6 ወር እስከ 3 ዓመት ከሰባት ወር እና ከአራት ሺሕ ብር እስከ ሰባት ሺሕ ብር ቅጣት የተወሰነባቸው ሲሆን፤ ነገር ግን የእስራት ቅጣቱ በ50 ሺሕ ብር ዋስ በሁለት ዓመት እግድ ተቀይሮላቸው ከእስር እንደለቀቁ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

አቶ ታደሰ ካሳ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ከአቶ በረከት ስምኦን ጋር በተመሠረተባቸው ተመሳሳይ ክስ የስምንት ዓመት ጽኑ እስራትና 15 ሺሕ ብር መቀጣታቸው አይዘነጋም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!